በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ...

image description
- ክስተቶች News    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራ አባይ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ  አመራሮች የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮን የሪፎርም ስራዎች እየጎበኙ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራ አባይ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ  አመራሮች የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮን የሪፎርም ስራዎች እየጎበኙ ነው፡፡

ቢሮው በከተማ አስተዳዳሩ ሪፎርም እንዲያደርጉ ከተለዩ 16 ተቋማት አንዱ ሲሆን ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ በ7 ዘርፎች ላይ ሪፎርም በማድረግ ከ40 በላይ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በመታገዘ በዘመናዊ መንገድ እየሰጠ ይገኛል፡፡

ይህም  ብልሹ አሰራርን ሙሉ በሙሉ ከመቅርፉም በላይ የተገልጋዩን ጊዜና ወጭ በመቆጠብ ከእንግልት መታደግ የቻለ ነው፡፡ይህን የሪፎርም ስራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጉብኝተውታል፡፡በዛሬው ዕለትም ከ6 መቶ በላይ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ይህንኑ የሪፎርም ስራ እየጎበኙ ነው፡

ለጎብኝዎቹ አቀባበል ያደረጉት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው  የተደረገው ተቋማዊ  ሪፎርም የህብረተሰቡን የዘመናት እንግልትና እሮሮ በመቅረፍ ሌሎች ተቋማትም ልምድ የሚቀምሩበት መሆን ችሏል ሲሉም ተናግረዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.