
የ5ኛዉ ዙር መሬት ሊዝ ጨረታ ማራዘሚያ ማስታወቂያ
የ5ኛዉ ዙር መሬት ሊዝ ጨረታ ማራዘሚያ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ፣ በየካ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤በኮልፌ ቀራንዮ ፤በአቃቂ ቃሊቲ፤በአዲስ ከተማ፣በጉለሌ፣ቂርቆስ፣ እና ለሚኩራ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ የካቲት 29/2017ዓም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማሳተም ከመጋቢት 01/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 12/2017ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ እያከናወነ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጅ የጨረታ ሰነድ ሽያጩን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እስከ መጋቢት 26/2017ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ ሽያጩ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፡-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት የቴሌ ብር አካዉንት በመክፈት ከአካዉንታችሁ ተቀናሽ በማድረግ ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን በ(2merkato.com link:- https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) በመግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነድ ሽያጩ እስከ መጋቢት 26/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን እያሳወቅን ተጫራቾች ቦታዎቹን በቀን 16/07/2017ዓ.ም፣18/07/2017ዓ.ም እና 23/07/2017ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰአት እና ከሰአት 8፡00 ሰአት በየክ/ከተማዉ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት ጉብኝት ማድረግ የሚቻል መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ፣የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኢንቨሎፕ በማሸግ መጋቢት 26/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 29/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የካቲት 29/2017 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ የማስተካከያ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር የመሬት ልማትና አስተዳደር የአምስተኛ (5ኛ) ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለማካሄድ በ9 ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ መፈለጉን በመግለጽ የካቲት 29/2017ዓ.ም በታተመ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ማስታወቂያ መገለፁ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቦታ ኮድ ማስተካከያ የተደረገበት፣ በኮልፌ፣በቂርቆስ እና በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተሞች ደግሞ የቦታ ስፋት፣ሕንፃ ከፍታ በመጨመሩ የአቅም ማሳያና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በተመሳሳይ ማስተካከያ ተደርጎበት ለጨረታ ከወጡ ቦታዎች መካከል ከዚህ በታች በሰኝጠረዡ ላይ በተቀመጠዉ አግባብ ተስተካክሏል፡፡
የቦታ ኮድ ማስተካከያ የተደረገባቸዉ ቦታዎች ዝርዝር | |||||
ተ.ቁ | የካቲት 29/2017ዓ.ም በታተመው ጋዜጣ ላይ የተገለጸበት ተራ ቁጥር | ክ/ከተማ | የካቲት 29/2017ዓ.ም በታተመ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ወጥቶ የነበረዉ የቦታ ኮድ | የተስተካከለዉ የቦታ ኮድ | ምርመራ |
1 | 145 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014170 | LDR-Aki-MIX-00014470 | |
2 | 146 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014171 | LDR-Aki-MIX-00014471 | |
3 | 147 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014172 | LDR-Aki-MIX-00014472 | |
4 | 148 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014173 | LDR-Aki-MIX-00014473 | |
5 | 149 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014174 | LDR-Aki-MIX-00014474 | |
6 | 150 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014175 | LDR-Aki-MIX-00014475 | |
7 | 151 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014176 | LDR-Aki-MIX-00014476 | |
8 | 152 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014177 | LDR-Aki-MIX-00014477 | |
9 | 153 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014178 | LDR-Aki-MIX-00014478 | |
10 | 154 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014179 | LDR-Aki-MIX-00014479 | |
11 | 155 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014180 | LDR-Aki-MIX-00014480 | |
12 | 156 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014181 | LDR-Aki-MIX-00014481 | |
13 | 157 | አቃቂ ቃሊቲ | LDR-Aki-MIX-00014182 | LDR-Aki-MIX-00014482 |
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.