በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬ...

image description
- ክስተቶች News    0

በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ሰነድ የሚከፈትበት ቀን ፕሮግራም

በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቅጥር ግቢ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሲካሄድ የዋለው 5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ መርሐ ግብር በስኬት ተጠናቋል ፡፡

ቢሮው በአምስተኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች የተዘጋጁ 427 ፕሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ከየካቲት 29/2017 እስከ መጋቢት 26/2017 ዓ.ም በኦንላይን ሰነድ ሲሸጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ይኸው የጨረታ ሰነድ ሰኞ መጋቢት 29/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ተጫራጮችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳርሽ ለተከታታይ የስራ ቀናት በይፋ የሚከፈት ይሆናል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.