ቢሮው የብቃት ምዘናን መሰረት ያደረገ የሰራተኛ...

image description
- ክስተቶች Uncategorized    0

ቢሮው የብቃት ምዘናን መሰረት ያደረገ የሰራተኛ ምዳባ ሊሰራ ነው ፡፡

********************************

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እየሰራ በሚገኘው ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ ሪፎርም ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሰራተኞችን በብቃት ምዘና መሰረት ምደባ እንደሚሰጥ በካፒታል ሆቴል ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ ገልፀዋል ፡፡

በመደረኩ የሰራተኞች ምደባ መመሪያ በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ በአቶ ኻሊድ ነስረዲን ቀርቦ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ፡፡ ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡ በቴክኖሎጂ እንዲዘምን ፣ ምቹ የስራ ቦታ ለሰራተኛ እና ለተገልጋይ ለማዘጋጀት እና ለብልሹ አሰራር መንስኤ የሆኑ መመሪያዎችን እያሻሻለ መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊዉ በቀጣይ ደግሞ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ ሰራተኞችን ምደባ እንደሚሰጥ ተናግረዋል ።

የሪፎርሙ ውጤታማነት የሚለካው አገልግሎት አሰጣጡ ከእጅ መንሻ የፀዳ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ሲቻል ነው ያሉት አቶ ኻሊድ በአመለካከትም ሆነ በቴክኒካል ብቃታቸዉ የበቁ ሰራተኞችን ለመመልመል ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥም ተናግረዋል ፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አቶ ተስፋዬ ጥላሁን በበኩላቸዉ ቀደም ሲል የተሰሩት ሪፎርሞች የተፈለገዉን ያህል ውጤት እንዳላመጡ ገልፀው ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት በፍትሐዊ መንገድ ማስተዳደር የሚያስችል ስር ነቀል ሪፎርም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክሎዉም የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች እስከ አሁን ያሳዩትን የትብብር መንፈስ በቀሪ የሪፎርም ስራዎች እስኪጠናቀቅ ድረስ በጋራ እንዲሰሩ አሳስበዋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.