የአዲስ አበባ ካቢኔ በ3ኛ አመት ፣ 7ኛ መደበኛ...

image description
- ክስተቶች Uncategorized    0

የአዲስ አበባ ካቢኔ በ3ኛ አመት ፣ 7ኛ መደበኛ ስብሰባ

የአዲስ አበባ ካቢኔ በ3ኛ አመት ፣ 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር፣ አገልግሎት አሰጣጥ ፣ የሰዉ ኃይል እና የአሰራር ጥልቅ ሪፎርሞ መተግበሪያ ረቂቅ ደንብ ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል።

ውድ እና ውስን የሆነውን የከተማዋን መሬት ለማስተዳደር እና የከዚህ በፊት የአሰራር ችግሮችን በተደራጁ እና ብቁ በሆነ ሙያተኛ ሊያደራጁ የሚችሉ ፤ ዘመናዊ የአሰራር ዘዴን በሚያሳልጡ እና ብልሹ አሰራርን ሊከላከሉ የሚችሉ የህግ ማዕቀፎችን መርምሮ በማፅደቅ እና ትግበራው በጠንካራ ዲሲፕሊን እንዲመራ ውሳኔ አሳልፏል።

በሌላ በኩል የአብርሆት ቤተ መፅሀፍት እና የጥቁር ህዝቦች ድል የሆነው የአድዋ ዐዐ ኪሎ ሜትር ሙዝየም ፕሮጀክት በአንድ የህግ ማዕቀፍ ማስተዳደር የሚቻልበትን ረቂቅ ደንብ መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.