የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የበጀት ዓመቱን ቅንጅታዊ ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ
ተቀናጅቶ መስራት ለውጤት እንደሚያበቃ ከከተማው አስተዳደሩ የኮሪደር ልማት ልምድ መቅሰም ያስፈልጋል …. አቶ ዘሪሁን ቢቂላ
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በካፒታል ሆቴል በመገምገም የትኩረት አቅጣጫዎችን አመላክተዋል፡፡የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተቀናጀ የመሬት መረጃና ማህደር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ቢቂላ መድረኩ የተዘጋጀው መርሀ ግብር ለማሟላት ሳይሆን በአተገባበር ወቅት ያጋጠመው ውስንነተቶችን በመለየት በቀጣይ የመፍትሔ ሀሳቦችን ለማመላከት ነው ብለዋል፡፡
በመድረኩ የመወያያ ሰነድ በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሪት ፀጋ ጉደታ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በቀረበው ሰነድ ዙሪያ አስተያየት የሰነዘሩት ተሳታፊዎች እንደገለፁት የመሬት ልማት አሰተዳደር ቢሮ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የተሰራው ስራ በተለይ ከሰነድ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ህገወጥ አሰራርን የሚቀርፍ በመሆኑ የሚደነቅ እና ለሌሎችም ተቋማት ጭምር ምሳሌ የሚሆን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ አክለውም ለልማት ተነሺዎች በወቅቱ ምትክ ቦታ አለማዘጋጀት እና በተቋማት መካከል ያለው የመረጃ ልውውጥ ደካማ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ እንዲሻሻል ጠይቀዋል፡፡
ከመድረኩ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት የተቀናጀ የመሬት መረጃና ማህደር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ቢቂላ በቢሮ በኩል የታዩ ችግሮች በቀጣይ እንደሚታረሙ ገልፀው ተቀናጅቶ መስራት ለውጤት እንደሚያበቃ በከተማው አስተዳደሩ እየተተገበረ ካለው የኮሪደር ልማት ልምድ ቀስመን ተናበን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትን ጨምሮ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
በአብዮት ታዬ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.