በደላላ የታጠረውና አገልግሎቶቹ የመልካም አስተዳደር ችግር የነበሩበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ባደረገው ሪፎርም አሰራሩን ከእጅ ንኪኪ ነፃ በማድረግ ሪፎርምን በተግባር ያረጋገጠ ተቋም ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወረዳና የክፍለ ከተማ አመራሮች ገለፁ።
በደላላ የታጠረውና አገልግሎቶቹ የመልካም አስተዳደር ችግር የነበሩበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ባደረገው ሪፎርም አሰራሩን ከእጅ ንኪኪ ነፃ በማድረግ ሪፎርምን በተግባር ያረጋገጠ ተቋም ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወረዳና የክፍለ ከተማ አመራሮች ገለፁ።
አመራሮቹ ይህን ያሉት የቢሮውን የሪፎርም ስራ ተዟዙረው በጎበኙበት ወቅት ነው።
ጥቅምት 17/207 (መልአ)=-
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናቀቀው በጀት ሪፎርም ካደረጉ ተቋማት መካከል አንዱ ነው።
በቢሮው ሪፎርም ማድረግ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት የነበረው ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ አገልግሎት አንፃር በርካታ ተገልጋዮች የሚስተናገድበትና ከአሰራሩ አለመዘመን ጋር ተያይዞ የመልካም አስተዳደር ችግር ይነሳበት ስለነበር ነው።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ሪፎርም አድርጎ አሰራሩን በቴክኖሎጁ ማስደገፍ የቻለው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ይህም ከ40 በላይ አገልግሎቶችን በዘመናዊ መንገድ እንዲሰጥ አስችሎታል።
የተቋሙን ትላንት መነሻ በማድረግ የዛሬው የሪፎርም ስራ ያስመዘገበው ውጤትም በተለያዩ ጊዜያት በከተማ አስተዳደሩ ፣በሚኒስተር መስሪያ ቤትና በክልል አመራሮች ተጎብኝቷል።
በዛሬው ዕለት ይህንኑ የሪፎርም ስራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሦስተኛ ዙር ስልጣኞቾ በቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ፣በጽ/ቤት ኃላፊ እና በባለሙያዎች ገለፃ ተደርጎላቸው የሪፎርም ስራዎችን ተዟዙረው በተግባር ጎብኝተዋል።
ጎብኝዎቹ ጉብኝቱን ተከትሎ ለቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀድም የቢሮ አገልግሎት በደላላ የታጀበ፣የተጓተተ፣ያለ እጅ መንሻ የማይከወን፣መረጃዎች የሚጠፉበትና ኃላ ቀር እንደነበር ገልፀዋል።
ዛሬ ግን እንደ ቢሮ የተደረገው ሪፎርም የተቋሙን ገጽታ ሙሉ በሙሉ መቀየር ችሏል ብለዋል።
ሪፎርሙን በተግባር ተዟዙረው የጎበኙት አስተያየት ሰጭዎቹ ሪፎርሙ ደላላን ሙሉ በሙሉ ከማስቀረቱም ባለፈ ከእጅ ንኪኪ ነፃ፣ኦን ላይ መሆን መቻሉም የተገልጋዩን ጊዜ፣ገንዘብና ጉልበት በመቆጠብ የተገልጋይ እንግልትን ያስቀረ በጥቅሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የቀረፈ ነው ብለዋል።
በተቋሙ ያዩትን የሪፎርም ውጤት በየስራ ዘርፋቸው እንደሚተገብሩትም ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.