የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስትራቴጂክ ካውን...

image description
- ክስተቶች News    0

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተዘጋጀው የአንድ ወር ዕቅድ ዙሪያ ምክክር በማድረግ እቅጣጫ አስቀመጡ፡፡

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተዘጋጀው የአንድ ወር ዕቅድ ዙሪያ ምክክር በማድረግ እቅጣጫ አስቀመጡ፡፡

ታህሳስ 23/2017 (መልአ) 
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ተቋማዊ ሪፎርም ያደረገው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሲንከባለል የመጣውን የህብረተሰቡን የዓመታት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ እየተፈታ ይገኛል፡፡ 

ለአብነትም ለበርካታ ዓመታት የተቋረጠው የመሬት ሊዝ ጨረታ በየሶስት ወሩ እንዲወጣ በማድረግ፣ የቀበሌ ቤቶችን፣ የአርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጆችን የይዞታ ማረጋጋጫ ካርታ አዘጋጅቶ በማሰራጨት፣ የከተማውን ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ እንቅስቃሴ የሚያፋጥኑ የለሙ መሬቶችን አዘጋጅቶ በማስተላለፍ እንዲሁም የመልሶ ማልማት ስራዎችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ መቻሉ ለማሳያነት ማንሳት ይቻላል፡፡

በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው የሚመራው የተቋሙ ስትራቴጅክ ካውንስል አባላት ይህንኑ ተግባር ለማስቀጠልና የህብረተሰቡን አንገብጋቢ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመሰጠት በቢሮው በተዘጋጀው የአንድ ወር ዕቅድ ዙሪያ ምክክር አካሂደዋል፡፡ 

በዚሁ መሰረት የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ቀልጣፋ አገልግሎት በሚያገኙበት አሰራር ፤ የመብት ፈጠራ ስራዎችና የአርሶ አደሩን የልማት ጥያቄዎች በተዘጋጀው ቀነ ገደብ ምላሽ እንዲያገኙ ምክክር በማካሄድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.