በይዞታቸው ላይ የማልማት ጥያቄ ያቀረቡ 31 አርሶ አደሮች ሊዋዋሉ ነው፡፡
ፕሬስ ሪሊዝ
በይዞታቸው ላይ የማልማት ጥያቄ ያቀረቡ 31 አርሶ አደሮች ሊዋዋሉ ነው፡፡
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም (መልአ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ16.75 ሄ/ር መሬት ላይ የማልማት ጥያቄ አቅርበው እንዲያለሙ የተፈቀደላቸውን 31 አርሶ አደሮች ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ሊያዋውል ነው፡፡
የከተማውን ስታንዳርድ በጠበቀ መልኩ አርሶ አደሮች በራሳቸው ይዞታ በተናጠልም ሆነ በጋራ እንዲያለሙ በህግ በተደነገገው መሰረት በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ዙር የማልማት ጥያቄ አቅርበው በቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፕሮጀክታቸው ታይቶ እንዲያለሙ ከተፈቀደላቸው 31 አርሶ አደሮች ጋር ርክክብ እና ውል የማዋዋል ስነ-ስርዓት በዕለቱ የሚካሂድ ይሆናል፡፡
አርሶ አደሮቹ በማኑፋክቸሪንግ፣ በትምህርት፣ በእርሻ፣ በሪል እስቴት እንዲሁም በሌሎች ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ዘርፎች ለመሰማራት ጥያቄ አቅርበው የተፈቀደላቸው ናቸው፡፡ በቀጣይም ቢሮው ተመሳሳይ የማልማት ጥያቄ የሚያቀርቡ አርሶ አደሮችን ለማስተናገድ ቁርጠኛ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ ይወዳል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.