አርሶ አደሮቹ ወደ ስራ ለመሰማራት የሚያስችላቸው...

image description
- ክስተቶች News    0

አርሶ አደሮቹ ወደ ስራ ለመሰማራት የሚያስችላቸው የውል ስምምነት ተፈራረሙ።

አርሶ አደሮቹ ወደ ስራ ለመሰማራት የሚያስችላቸው የውል ስምምነት ተፈራረሙ።

የዘመናት ጥያቄያችን ምላሽ በማግኘቱ ተደስተናል፡፡አርሶ አደሮቹ

ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም (መልአ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በይዞታቸው ላይ የማልማት ጥያቄ አቅርበው የተፈቀደላቸው 31 አርሶ አደሮች ጋር ወደ ስራ መግባት የሚያስችል ውል ተፈራርሟል።

አርሶ አደሮቹ የከተማውን ስታንዳርድ በጠበቀ መልኩ 16.75 ሄክታር መሬት ላይ በማኑፋክቸሪንግ፣ በሪል ስቴት፣ በትምህርት እና በሌሎች ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው የስራ መስኮች ለመሰማራት ጥያቄ አቅርበው የነበሩ ናቸው። 

በውል ስምምነት መረሃ ግብሩ ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ቢሮው የዘመናት ጥያቄያቸውን ምላሽ በመስጠቱ መደሰታቸውን ገልፀው በአጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚገቡም ተናግረዋል።

የአርሶ አደሮቹ ጥያቄ ከፍተኛ የሆነ የቢዝነስ ሀሳቦችን የያዘና ለከተማው ነዋሪም ጭምር ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ነው ያሉት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኻሊድ ነስረዲን ሌሎች የከተማው አርሶ አደሮችም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቢኖራቸው በተቀመጠው ደንብና መመሪያ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል ብለዋል።
አክለውም መንግስት በቀጣይም የአሮሶ አደሩን ህይወት በሚቀይር ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.