የመብት ፈጠራና ይዞታ አገልግሎት ዘርፍ
ምክትል ቢሮ ኃላፊ:
የኑስ አደም
የመብት ፈጠራ እና ይዞታ አገልግሎት ዘርፍ ተግባርና ኃላፊነት ተጠሪነቱ ለመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል 1.የዘርፉን ስትራቴጂክ ዕቅድ ከቢሮው ጋር ተናባቢ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጅ ያደርጋል አተገባበሩን ይመራል ይከታተላል 2.ለዘርፉ የተመደበውን በጀት እና ግብዓት በአግባቡ ስራ ላይ ያውላል/እንዲውል ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል 3.የይዞታ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት በመመዝገብ ለመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እስኪተላለፍ ድረስ ጥበቃ ያደርጋል፤ የቦታ ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ 4.የመሬት ይዞታ እና የቤት አጠቃቀም ዓይነትና የባለይዞታዎች መረጃ ይይዛል፤ ይጠብቃል፤ አግባብ ባለው ህግ መሠረት ለህጋዊ ባለይዞታዎች የቦታ አገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎች መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፤ 5.አግባብ ባለው ህግ መሠረት የነባር ቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን አስልቶ ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ያስተላልፋል፤ 6.ከካሳ ጉዳይ በስተቀር ለግብር ሰብሳቢ ተቋማትና ለሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት የማይንቀሳቀስ ንብረት ግምት አገልግሎት ይሰጣል፤ 7.መደበኛ የይዞታ አገልግሎቶችን ያከናውናል፤ ህጋዊ ያልሆነ የይዞታ አስተዳደር አፈፃፀም ሲከሰት የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፡፡ 8.በህግ የሚቀመጠውን የአሰራር ሥርአት ተከትሎ እና በከተማ አስተዳደሩ ለሚፈቀድላቸው፣ ለሰነድ አልባ ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ ማህደራቸውን ያደራጃል፤ 9.በዘርፉ በየደረጃው ለሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል ተገቢውን ምላሽ በወቅቱ ይሰጣል እንዲሰጥ ያደርጋል 10.በዘርፉ በየደረጃው ያሉ የአሰራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በመለየት የክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል ግብረ-መልስ ይሰጣል አተገባበሩን ይከታተላል ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል/እንዲወሰድ ያስደርጋል 11.በዘርፉ ስር ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ከአሰራር አንፃር በመመርመር ውሳኔ ይሰጣል/እንዲሰጥ ያስደርጋል፡፡ 12.መደበኛ የይዞታ አገልግሎት እና የመብት ፈጠራ ስራዎች በከተማ አስተዳደሩ በጸደቀው ቴክኖሎጂ (ሲስተም) እንዲፈጸም ያስተባብራል፣ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጣል፣ 13.የዘርፉ ስር ያሉ በየደረጃው ያሉ የስራ ክፍሎችን አፈፃጸም በጋራ ይደግፋል፣ ይገመግማል ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል
በዘርፉ ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች:
ምንም አልተገኘም.