ቢሮ ኃላፊ
ምክትል ቢሮ ኃላፊ:
አቶ ሲሳይ ጌታቸው
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት 1.የከተማ መዋቅራዊ ፕላን እና ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላኖች መሰረት በማድረግና ፍትሃዊና ኢኮኖሚያዊ የመሬት ልማትና አቅርቦት እንዲሁም የከተማ ማደስ ጥናት ስራዎችን ያከናውናል፤ እንዲከናወን ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ 2.የልማት ቅደም ተከተል በማውጣት የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጥናት፣ መርሀ ግብሮች፣ ጥቅል ዓላማዎች፣ ግቦች፣ የኢንቨስትመንት ዕቅዶች፣ በጀት፣ የዓላማ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎችና የጊዜ ሠሌዳ ያዘጋጃል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ 3.ለመልሶ ማልማትና ለመሬት ዝግጅት ተፈላጊው መሰረተ ልማት እንዲጠና ለሚመለከታቸው አካላት ያሳውቃል፤ መጠናቱን ያረጋግጣል፤ ከገንቢዎች በሚገኝ ግብዓት የግንባታ ቅንጅት እቅድና በጀት ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድም ያስገነባል፤ 4.የመሬት አቅርቦትና ፍላጎት ሚዛኑን ጠብቆ መሄድ እንዲችል የተለያዩ ጥናቶችን በማከናወን የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ 5.በከተማ ማዕከላትና ኮሪደሮች በአካባቢ ልማት ፕላን መሰረት የተቀናጀ የከተማ ንድፍ ያዘጋጃል/እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በሚመለከተው አካል ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ 6.ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች የሚውል መሬት ወሰን ያስከብራል፤ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤ 7.በከተማው ውስጥ የተጎዱና ያረጁ አካባቢዎችን ለማደስ እንዲቻል የካሳ ክፍያ ስርዓት ጥናት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያከናውናል፤ በየጊዜውም እንዲሻሻል ያደርጋል፤ የነዋሪዎቹን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ ሁኔታ ስታንዳርዱን ጠብቆ መልሶ ማልማት የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል፤ 8.ለግንባታ ተረፈ ምርት መድፊያነት አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎችን አስመልክቶ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ 9.የልማት ተነሺዎች የምትክ ቤት ፍላጎት ያጠናል፤ የምትክ ቤት መቀበያ ሰርተፊኬት ይሰጣል፤ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤ ሲፈቀድም ለተነሽዎች ምትክ ቤት ድልድል በማድረግ እንዲሰጣቸው ለቤቶች ኮርፖሬሽን ያስተላልፋል፤ የተሰጣቸው መሆኑን ያረጋግጣል፤ 10.ለልዩ ልዩ የልማት ስራዎች የለማ መሬት፣ በይዞታነት ለማንም አካል ያልተላለፉ የተዘጋጁና ያልተዘጋጁ ቦታዎችን፣ ባንክ የተደረጉ ክፍት መሬቶችን ወይም ይዞታዎችን ይመዘግባል፤ በዲጂታል እና በፕላን ፎርማት ተገቢውን መረጃ ይይዛል፤ የቦታውንም አገልግሎት ደረጃ እና አስፈላጊ መግለጫዎችን የያዘ የመለያ ሰሌዳ ይተክላል፤ የቦታዎቹን ዝርዝር መረጃ ለደንብ ማስከበር ኤጀንሲ ያስተላለፋል፤ ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር ለሕገወጥነት እንዳይጋለጡ ያደርጋል፤ 11.በከተማው አስተዳደር ወሰን ክልል ውስጥ ያለውን የመሬት ሃብት ኦዲት ያደርጋል፤ በኦዲት ግኝቱ መሠረት ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤ 12.የይዞታ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት በመመዝገብ ለመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እስኪተላለፍ ድረስ ጥበቃ ያደርጋል፤ የቦታ ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ 13.በካርታ በተደገፈ መልኩ የከተማ ቦታ ደረጃ፣ የሊዝ መነሻ ዋጋ እና አማካይ የሊዝ ዋጋ ጥናት ያካሂዳል፤ ወቅታዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ 14.በከተማ ክልል ወስጥ ለልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች የለማ መሬትን በመመዝገብ ወጥ የሽንሻኖ ቁጥር ይሰጣል፤ በጨረታ እና በምደባ የሚተላለፉ ቦታዎችን ይለያል፤ ቦታው ለተጠቃሚ እስከሚተላለፍ ድረስ ከደንብ ማስከበር ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት የመከላከልና የመጠበቅ ሥራ ያከናውናል፤ 15.መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው የተዘጋጁ የከተማ ቦታዎች ለአልሚዎች የሚተላለፉበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ አግባብ ባለው ህግ መሠረት መሬት ለባለመብት ያስተላልፋል፤ ቦታውን በመስክ ያስረክባል፤ በሊዝ ህግና ዉል መሠረት የሊዝ ክፍያ ይሰበስባል፤ 16.አግባብ ባለው ህግና የሊዝ ውል መሠረት ግንባታ መከናወኑን ያረጋግጣል፤ በሕግና በውል በተወሰነው ጊዜና ሁኔታ መሬቱ መልማቱን ያረጋግጣል፤ የሊዝ ውል ማሻሻያ ያደርጋል፣ መሬቱ ካለማ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ 17.ለጊዜያዊ መጠቀሚያነት አገልገሎት የሚሰጡ ቦታዎችን በጊዜያዊ የሊዝ ውል ያስተላልፋል፤ የውል ጊዜያቸው ወይም አገልግሎታቸው ሲያበቃ ቦታውን በመረከብ ለዳግም ልማት ያዘጋጃል፤ 18.ለልማት ይዞታቸውን የሚለቁ ባለይዞታዎች ከመልቀቃቸው በፊት አግባብ ባለው ህግ መሰረት የይዞታ ማስለቀቅ ሂደቱን ይተገብራል፤ የተነሽ አርሶ አደሮችን ዝርዝር እና መረጃ ለአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ያስተላልፋል፤ 19.የልማት ተነሺዎች ይዞታቸውን ከመልቀቃቸው በፊት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የምትክ ቦታ፣ ቤት፣ ተመጣጣኝ የንብረት ካሳ እና ሌሎች ክፍያዎች የሚያኙበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ ለልማት በሚለቀቀው መሬት ላይ ላለው ንብረት በህግ መሠረት ካሳ ይተምናል፤ እንዲተመን ያደርጋል፤ የንብረት ካሳና ሌሎች ክፍያዎችን ይፈጽማል፤ ምትክ ቦታ ያዘጋጃል፤ ምትክ ቦታ ያስተላልፋል፤ 20.ለመሠረተ ልማት አውታር፤ ለመናፈሻ፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ለሕዝብ መሰብሰቢያ ፕላዛዎች በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ቦታ ያዘጋጃል፤ ያስተላልፋል፤ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ 21.ለልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች ሊያገለግሉ የሚችሉ የማዕድን ማውጫ ቦታዎች በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ከልሎ ይይዛል፤ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተሰጠ የማዕድን ማዉጫ ፈቃድ መሠረት በጊዜያዊ የሊዝ ውል መሬቱን ያስተላልፋል፤ የማእድን ማውጣት ሥራው ሲጠናቀቅ ወይም ፈቃዱ ሲሰረዝ ወይም የሊዝ ውሉ ጊዜ ሲያበቃ መሬቱን በመረከብ ለዳግም ልማት ያዘጋጃል፤ 22.የመሬት ይዞታ እና የቤት አጠቃቀም ዓይነትና የባለይዞታዎች መረጃ ይይዛል፤ ይጠብቃል፤ አግባብ ባለው ህግ መሠረት ለህጋዊ ባለይዞታዎች የቦታ አገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎች መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፤ 23.አግባብ ባለው ህግ መሠረት የቤት/ህንጻ የጣራና ግድግዳ ግብር ተመን ያሰላል /እንዲሰላ ያደርጋል ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ያስተላልፋል፤ 24.ለግብር ሰብሳቢ ተቋማት፣ ለፍርድ ቤቶችና ለሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት የማይንቀሳቀስ ንብረት ግምት አገልግሎት ይሰጣል፤ 25.መደበኛ የይዞታ አገልግሎቶችን ያከናውናል፤ ህጋዊ ያልሆነ የይዞታ አስተዳደር አፈፃፀም ሲከሰት የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፡፡ 26.በህግ የሚቀመጠውን የአሰራር ስርአት ተከትሎ መብት ላልተፈጠረላቸው ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በማዘጋጀት በቋሚ መዝገብ በመመዝገብ ለባለይዞታው ይሰጣል፤ ማህደራቸውን ያደራጃል፤ ከሕግ ውጪ የተሰጠ የቦታ ይዞታ ወይም የቤት ባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ያግዳል፣ እንደአስፈላጊነቱ ይሰርዛል/ያመክናል/፤ 27.የቦታ ይዞታ እና/ወይም የቤት ይዞታ ካርታ ኮፒዎችን በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤ የይዞታ ሰነዶችን በማደራጀት ለመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ያስተላልፋል 28.ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታቸውን የለቀቁ ተነሺዎችን መልሰው በዘላቂነት ያቋቁማል፤ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ፡- ሀ) የማቋቋሚያ ማዕቀፍ ይቀርጻል፤ ለከንቲባ ያቀርባል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ለ) የልማት ሥራው በሚሰራበት ወቅት ተነሺዎች በተቻለ መጠን የስራ እድል እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ሐ) የተነሺዎችን የኢንቨስትመንት ሼር ባለቤትነት መብት ያስከብራል፤ ተጠቃሚ መሆናቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ መ) የልማት ተነሺዎች የኢንቨስትመንት ባለቤት የሚሆኑበትን የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፤ ሠ) ሌሎች አግባብ ባላቸው ሕግ ደንብና መመሪያ የተገለጹትን ተግባራትና ኃላፊነቶች ይፈጽማል፡፡ 29. በየደረጃው ያለውን የቢሮ ዘርፎችን፣ ዳይሬክቶሬቶችን ፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራር እና ባለሙያዎችን ህግና አሰራርን ተከትሎ ያሾማል/ይመድባል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል /ያስወስዳል፣
በዘርፉ ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች:
የተነሺዎች መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስልጣን፣ ተግባር...
iconየመሬት ሀብትና የአሰራ ጥራት ኦዲት ዳይሬክቶሬት
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስልጣን፣ ተግባር...
iconጽ/ቤት ኃላፊ
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስልጣን፣ ተግባር...
icon