የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ
ምክትል ቢሮ ኃላፊ:
ደስታ መርጋ
የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ ተግባርና ኃላፊነት 1.የዘርፉን ስትራቴጂክ ዕቅድ ከቢሮው ጋር ተናባቢ በሆነ ምልኩ እንዲዘጋጅ ያደርጋል አተገባበሩን ይመራል ይከታተላል፤ 2.ለዘርፉ የተመደበውን በጀት እና ግብዓት በአግባቡ ስራ ላይ ያውላል/እንዲውል ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 3.ለመልሶ ማልማትና ለመሬት ዝግጅት ተፈላጊው መሰረተ ልማት እንዲጠና ለሚመለከታቸው አካላት ያሳውቃል፤ መጠናቱን ያረጋግጣል፤ ከገንቢዎች በሚገኝ ግብዓት የግንባታ ቅንጅት እቅድና በጀት ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድም ያስገነባል፤ 4.ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች የሚውል መሬት ወሰን ያስከብራል፤ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤ 5.በከተማው ውስጥ የተጎዱና ያረጁ አካባቢዎችን ለማደስ እንዲቻል የካሳ ክፍያ ስርዓት ጥናት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያከናውናል፤ በየጊዜውም እንዲሻሻል ያደርጋል፤ የነዋሪዎቹን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ ሁኔታ ስታንዳርዱን ጠብቆ መልሶ ማልማት የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል፤ 6.ለግንባታ ተረፈ ምርት መድፊያነት አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎችን አስመልክቶ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ 7.የልማት ተነሺዎች የምትክ ቤት ፍላጎት ያጠናል፤ የምትክ ቤት መቀበያ ሰርተፊኬት ይሰጣል፤ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤ ሲፈቀድም ለተነሽዎች ምትክ ቤት ድልድል በማድረግ እንዲሰጣቸው ለቤቶች ኮርፖሬሽን ያስተላልፋል፤ የተሰጣቸው መሆኑን ያረጋግጣል፤ 8.ለልዩ ልዩ የልማት ስራዎች የለማ መሬት፣ በይዞታነት ለማንም አካል ያልተላለፉ የተዘጋጁና ያልተዘጋጁ ቦታዎችን፣ ባንክ የተደረጉ ክፍት መሬቶችን ወይም ይዞታዎችን ይመዘግባል፤ በዲጂታል እና በፕላን ፎርማት ተገቢውን መረጃ ይይዛል፤ የቦታውንም አገልግሎት ደረጃ እና አስፈላጊ መግለጫዎችን የያዘ የመለያ ሰሌዳ ይተክላል፤ የቦታዎቹን ዝርዝር መረጃ ለደንብ ማስከበር ኤጀንሲ ያስተላለፋል፤ ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር ለሕገወጥነት እንዳይጋለጡ ያደርጋል፤ 9.በካርታ በተደገፈ መልኩ የከተማ ቦታ ደረጃ፣ የሊዝ መነሻ ዋጋ እና አማካይ የሊዝ ዋጋ ጥናት ያካሂዳል፤ ወቅታዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ 10.በከተማ ክልል ወስጥ ለልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች የለማ መሬትን በመመዝገብ ወጥ የሽንሻኖ ቁጥር ይሰጣል፤ በጨረታ እና በምደባ የሚተላለፉ ቦታዎችን ይለያል፤ ቦታው ለተጠቃሚ እስከሚተላለፍ ድረስ ከደንብ ማስከበር ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት የመከላከልና የመጠበቅ ሥራ ያከናውናል፤ 11.መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው የተዘጋጁ የከተማ ቦታዎች ለአልሚዎች የሚተላለፉበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ አግባብ ባለው ህግ መሠረት መሬት ለባለመብት ያስተላልፋል፤ ቦታውን በመስክ ያስረክባል፤ በሊዝ ህግና ዉል መሠረት የሊዝ ክፍያ ይሰበስባል፤ 12.አግባብ ባለው ህግና የሊዝ ውል መሠረት ግንባታ መከናወኑን ያረጋግጣል፤ በሕግና በውል በተወሰነው ጊዜና ሁኔታ መሬቱ መልማቱን ያረጋግጣል፤ መሬቱ ካለማ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ 13.ለጊዜያዊ መጠቀሚያነት አገልገሎት የሚሰጡ ቦታዎችን በጊዜያዊ የሊዝ ውል ያስተላልፋል፤ የውል ጊዜያቸው ወይም አገልግሎታቸው ሲያበቃ ቦታውን በመረከብ ለዳግም ልማት ያዘጋጃል፤ 14.ለልማት ይዞታቸውን የሚለቁ ባለይዞታዎች ከመልቀቃቸው በፊት አግባብ ባለው ህግ መሰረት የይዞታ ማስለቀቅ ሂደቱን ይተገብራል፤ የተነሽ አርሶ አደሮችን ዝርዝር እና መረጃ ለአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ይልካል፤ 15.በዘርፉ በየደረጃው ያሉ የአሰራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በመለየት የክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል ግበረ መልስ ይሰጣል አተገባበሩን ይከታተላል ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል/እንዲወሰድ ያስደርጋል 16.ለልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች ሊያገለግሉ የሚችሉ የማዕድን ማውጫ ቦታዎች በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ከልሎ ይይዛል፤ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተሰጠ የማዕድን ማዉጫ ፈቃድ መሠረት በጊዜያዊ የሊዝ ውል መሬቱን ያስተላልፋል፤ የማእድን ማውጣት ሥራው ሲጠናቀቅ ወይም ፈቃዱ ሲሰረዝ ወይም የሊዝ ውሉ ጊዜ ሲያበቃ መሬቱን በመረከብ ለዳግም ልማት ያዘጋጃል፤ 17.በዘርፉ ስር ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ከአሰራር አንፃር በመመርመር ውሳኔ ይሰጣል/እንዲሰጥ ያስደርጋል፤ 18.በቢሮው በየደረጃው ለሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል ተገቢውን ምላሽ በወቅቱ ይሰጣል እንዲሰጥ ያደርጋል፤ 19.የዘርፉ ስር ያሉ በየደረጃው ያሉ የስራ ክፍሎችን አፈፃጸም በጋራ ይደግፋል፣ ይገመግማል ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፤
በዘርፉ ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች:
ምንም አልተገኘም.