የለማ መሬት ማስተላለፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
አቶ ጫሊ አብርሀም
የለማ መሬት ማስተላለፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት ተጠሪነቱ ለመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤ 1.የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ ከዘርፉ ጋር ተናባቢ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጅ ያደርጋል በስሩ ላሉ ቡድኖች/ባለሙያዎች በተናበበ መልኩ ያወርዳል አተገባበሩን ይመራል ይከታተላል፤ 2.ለዳይሬክቶሬቱ የተመደበውን በጀት እና ግብዓት በአግባቡ ስራ ላይ ያውላል/እንዲውል ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 3.በካርታ በተደገፈ መልኩ የከተማ ቦታ ደረጃ፣ የሊዝ መነሻ ዋጋ እና አማካይ የሊዝ ዋጋ ጥናት ያካሂዳል፤ ወቅታዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ 4.መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው የተዘጋጁ የከተማ ቦታዎች ለአልሚዎች የሚተላለፉበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ አግባብ ባለው ህግ መሠረት መሬት ለባለመብት ያስተላልፋል፤ ቦታውን በመስክ ያስረክባል/እንዲረከብ ያደርደጋል፤ በሊዝ ህግና ዉል መሠረት የሊዝ ክፍያ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፤ 5.አግባብ ባለው ህግና የሊዝ ውል መሠረት ግንባታ መከናወኑን ያረጋግጣል/እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤ በሕግና በውል በተወሰነው ጊዜና ሁኔታ መሬቱ መልማቱን ያረጋግጣል/እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤ መሬቱ ካለማ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ 6.ለጊዜያዊ መጠቀሚያነት አገልገሎት የሚሰጡ ቦታዎችን በጊዜያዊ የሊዝ ውል ያስተላልፋል፤ የውል ጊዜያቸው ወይም አገልግሎታቸው ሲያበቃ ቦታውን በመረከብ ለዳግም ልማት ያዘጋጃል፤ 7.ለልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች ሊያገለግሉ የሚችሉ የማዕድን ማውጫ ቦታዎች ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተሰጠ የማዕድን ማዉጫ ፈቃድ መሠረት በጊዜያዊ የሊዝ ውል መሬቱን ያስተላልፋል፤ የማእድን ማውጣት ሥራው ሲጠናቀቅ ወይም ፈቃዱ ሲሰረዝ ወይም የሊዝ ውሉ ጊዜ ሲያበቃ የሊዝ ውል አቅርጦ ለሚመለከተው የስራ ክፍል ያሳውቃል፤ 8.በምደባ እና በጨረታ የተዘጋጀውን የለማ መሬት በውሳኔ መሰረት የሊዝ ውል በማፅደቅ እና የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በማፅደቅ ያስተላልፋል፤ 9.በየደረጃው ያሉ የስራ ክፍሎችን አፈፃጸም በጋራ ይደግፋል፣ ይገመግማል ለዘርፉ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል ፤ 10.የግንባታ መጀመሪያና የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ፣የአገልግሎት ለውጥ እና የፕሮግራም ለውጥ የሊዝ ውል ማሻሻያ በሊዝ ህጉ እና ይህን ተከትሎ በሚሰጡ ውሳኔዎች መሰረት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያረጋግጣል አገልግሎት ይሰጣል/ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ 11.የግንባታ መጀመሪያ፣ ማጠናቀቂያ እና የዋጋ ለውጥ ላላቸው አገልግሎት ለውጥ ማሻሻያ ጠያቂዎች የውሳኔ ሀሳብ አዘጋጅቶ ያቀርባል ውሳኔ ሲያገኝ አገልግሎት ይሰጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል፤ 12.በውላቸው መሠረት ያላለሙ አልሚዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ 13.ከሊዝ ክፍያ ጋር ለሚቀርቡ ጥቄዎች ምላሽ ይሰጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል፣ የሊዝ ቅድመ ክፍያ እና የሊዝ ውል ማሻሻያ ቅጣት ማስከፈል እና የጊዜያዊ የሊዝ ውል ያለፈባቸውን ተከታትሉ ያስመልሳል/እንዲመለስ ያደርጋል፤ 14.በተለያየ ጊዜ በሊዝ አግባብ የተላለፉ ይዞታዎችን መረጃ እንዲደራጅ ያደርጋል/ያስደርጋል ለሚመለከተው የስራ ክፍል ያስተላልፋል/እንዲተላለፍ ያደርጋል፤ 15.በየደረጃው ያሉ የአሰራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በመለየት የክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል ግበረ መልስ ይሰጣል አተገባበሩን ይከታተላል ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል/እንዲወሰድ ያስደርጋል፤ 16.በየደረጃው ያሉ የስራ ክፍሎችን አፈፃጸም በጋራ ይደግፋል፣ ይገመግማል፣የአፈፃፀም ምዘና ያካሂዳል፣ ውጤቱን ተከትሎም ማበረታቻና ድጋፍ ያደርጋል፣ለዘርፉ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል ያደርጋል፤ 17.ሌሎች ከዘርፉ የሚሰጡትን ተግባራት ተቀብሎ ያከናውናል፤
የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት
መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ ታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!