የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
አቶ ተስፋዬ ጥላሁን
የመሬት ዝግጅትና ባንክና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት 1.የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ ከዘርፉ ጋር ተናባቢ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጅ ያደርጋል በስሩ ላሉ ቡድኖች/ባለሙያዎች በተናበበ መልኩ ያወርዳል ፤ አተገባበሩን ይመራል ፤ ይከታተላል ፤ 2.ለዳይሬክቶሬቱ የተመደበውን በጀት እና ግብዓት በአግባቡ ስራ ላይ ያውላል/እንዲውል ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል 3.በከተማው ቀልጣፋና ዘመናዊ የመሬት አቅርቦትና አሰጣጥ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት የሚያሠችል የመሬት የፍላጎት እና አቅርቦት ጥናቶችን ያካሄዳል ወይም እንዲካሄዱ ያደርጋል፤ 4.በከተማ ደረጀ የተዘጋጁ የመሬት አቅርቦት ጥናቶችን የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል ፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ 5.በከተማ ክልል ወስጥ ለልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች የለማ መሬትን በመመዝገብ ወጥ የሽንሻኖ ቁጥር ይሰጣል፤ በጨረታ እና በምደባ የሚተላለፉ ቦታዎችን ይለያል፤ ቦታው ለተጠቃሚ እስከሚተላለፍ ድረስ ከደንብ ማስከበር ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት የመከላከልና የመጠበቅ ሥራ ያከናውናል፤ 6.ለልዩ ልዩ የልማት ስራዎች የለማ መሬት፣ በይዞታነት ለማንም አካል ያልተላለፉ የተዘጋጁና ያልተዘጋጁ ቦታዎችን፣ ባንክ የተደረጉ ክፍት መሬቶችን ወይም ይዞታዎችን ይመዘግባል፤ በዲጂታል እና በፕላን ፎርማት ተገቢውን መረጃ ይይዛል፤ የቦታውንም አገልግሎት ደረጃ እና አስፈላጊ መግለጫዎችን የያዘ የመለያ ሰሌዳ እንዲተከል ድጋፍ ያደርጋል፤ የቦታዎቹን ዝርዝር መረጃ ለደንብ ማስከበር ኤጀንሲ መተላለፋቸውን ያረጋግጣል መረጃዎችን አደራጅቶ ይይዛል፤ ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ በመተባበር ለሕገወጥነት እንዳይጋለጡ ክትትል ያደርጋል፤ 7.ለመሠረተ ልማት አውታር፤ ለመናፈሻ፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ለሕዝብ መሰብሰቢያ ፕላዛዎች በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ቦታ ያዘጋጃል፤ ያስተላልፋል፤ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዲዘጋጅ ያደርጋል ፤ 8.የፀዳ መሬት እና ባዶ ቦታዎችን በመሰረታዊ ካርታ እንዲመዘገብ ክትትል ያደርጋል፤ 9.መሬት ሲተላለፍ መሰረታዊ ካርታ ላይ እንዲወራረስ በማድረግ እና ያልለማ መሬት በመለየት እንዲለማ ያደርጋል 10.የጸዳ መሬት እና ባዶ ቦታዎችን መረጃ በሀርድ ኮፒ እና ስካን አድርጎ በሶፍት ኮፒ እንዲደራጅ ያደርጋል፤ 11.የመንግስት ባዶ ቦታ ሆኖ ቤዝ ማፕ ላይ የተመዘገበ ቦታ በቢሮ ስም ቅድመ ካርታ እንዲዘጋጅለት ያደርጋል፣ 12.ለልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች ሊያገለግሉ የሚችሉ የማዕድን ማውጫ ቦታዎች በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ከልሎ ይይዛል የማዕድን ማውጣት ሥራው ሲጠናቀቅ ወይም ፈቃዱ ሲሰረዝ ወይም የሊዝ ውሉ ጊዜ ሲያበቃ መሬቱን በመረከብ ለዳግም ልማት ያዘጋጃል፤ 13.መሬት ለማዘገጀት የሚያስችል የከተማዋን ፕላን መሰረት የሽንሻኖ ስራ ያከናውናል/እንዲከናወን ድጋፍ ያደርጋል፤ 14.በፕላን መሰረት የተሸነሸነ ቦታ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤ 15.ለልማት የሚዘጋጁ ቦታዎችን በከተማ ፕላን ጥናት መነሻ የመሰረተ ልማት መስመር እንዲዘረጋ ያደርጋል 16.የልማት ተነሺዎች መልሶ የሚሰፍሩበት አከባቢ የመሰረተ ልማት እንዲዘረጋ ያደርጋል 17.በየደረጃው ያሉ የአሰራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በመለየት የክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል ግበረ መልስ ይሰጣል አተገባበሩን ይከታተላል ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል/እንዲወሰድ ያስደርጋል፤ 18. በየደረጃው ያሉ የስራ ክፍሎችን አፈፃጸም በጋራ ይደግፋል፣ ይገመግማል ለዘርፉ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል ያደርጋል፤ 19.የከተማውን የመሬት አቅርቦት ፍለጎት የሚያሻሻል የመሬት ዝግጅት ሥራን በማዕካል የተደራጁ ሦስቱን ቡድኖች ውጤታማ በሆነ መልክ ያሳማራል ፣
የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት
መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ ታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!