የከተማ ማዕከላት መልሶ ማልማት ትግበራና ክትትል ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
አቶ ጌታቸው ጥበቡ
የከተማ ማዕከላት መልሶ ማልማት ትግበራና ክትትል ዳይሬክቶሬት 1.የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ ከዘርፉ ጋር ተናባቢ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጅ ያደርጋል በስሩ ላሉ ቡድኖች/ባለሙያዎች በተናበበ መልኩ ያወርዳል አተገባበሩን ይመራል ይከታተላል፤ 2.ለዳይሬክቶሬቱ የተመደበውን በጀት እና ግብዓት በአግባቡ ስራ ላይ ያውላል/እንዲውል ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል 3.በከተማ ፕላን መነሻ የማዕካለትና ከሪደሮችን መረጃ በዝርዝር ይለያል 4.የልማት ቅደም ተከተል በማውጣት የማዕከላትና ኮሪደሮች ልማት ፕሮጀክት ጥናት፣ መርሀ ግብሮች፣ ጥቅል ዓላማዎች፣ ግቦች፣ የኢንቨስትመንት ዕቅዶች፣ በጀት፣ የዓላማ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎችና የጊዜ ሠሌዳ ያዘጋጃል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ 5.የከተማ መዋቅራ ፕላን መነሻ በማድረግ የአጭር፣የመካከለኛ እና ረጅም ጊዜ የማዕካለትና ከሪደሮች ልማት ዕቅድ ያዘጋጃል 6.የተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ባለድርሻን በማወያየት አማራጭ ፋይናንስ መንገዶች ይለያል እንዲሁም በልማት ተሳታፊዎችን የሆኑ ባለድርሻዎች ይለያል የዕቅዱ አካል ያደርጋል 7.በማዕካላትና ኮሪደሮች የመልሶ ማልማት ሥራ የሚተገበርባቸው ቦታዎች ልማት ቅደም ተከተል ያጠናል ወይም ያስጠናል 8.በጥናቱ መሰረት ቅደም ተከተል የወጣላቸው ቦታዎች በዝርዝር ከጥናቱ ሃሳቡ ጋር የመጨረሻ ዕቅድ አካል ይሆናል 9.የተዘጋጀው ዕቅድ እና የልማት ቅደም ተከተል ሰነድ በቢሮ ስትራቴጀክ ከውንስል ቀርቦ ውይይት እንዲደረግ ያደርጋል 10.የመጨረሻ ረቂቅ ዕቅድ በከተማው ካቢኔ እንዲጸድቅ አዘጋጅቶ ያቀርባል 11.በአጭር ጊዜ እንዲለሙ የተለዩ ወይም በቅደም ተከተል በመጀመሪያ ረድፍ እንዲለሙ የተለዩ ቦታዎች በአካባቢ ልማት ፕላን መሰረት የተቀናጀ የከተማ ንድፍ ጥናት ያካሄዳል ወይም እንዲካሄድ ያደርጋል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል ወይም እንዲተገበር ክትትል ያደርጋል 12.መልሶ የሚለሙ ቦታዎች ልማቱ ከመጀመሩ ከአንድ ዓመት በፊት በልማት አከባቢ ነዋሪ ጋር ወይይት ያደርጋል በልማቱ ላይ እንዲሳተፉ ግንዛቤ ይፈጥራል 13.ሕጋዊ የቦታ ባለይዞታዎችና ባለንብረቶች መብት በህግ መሰረት መከበሩ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የማዕካለትና ከሪደሮች ልማት አተገባበርን ይመራል እና አፈጻጸሙን ይከታተላል ፡፡ 14.የማዕከላትንና ኮርደሮችን ቦታዎች የሚመለከቱ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካለት ይረከባል፣ ይጠብቃል፣ ተገቢውን የዲጅታል እና የፕላን ፎርማት መረጃ ይይዛል፣ 15.በከተማ ማዕከላት እና በልማት ኮሪደሮች ክልል ውስጥ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናት ያካሄዳል/እንዲካሄድ ያደርጋል፤ 16.የማዕከላትና በኮሪደሮች ቦታዎች ለህገወጥ ወራራና ተግባር እንዳይጋለጡ ይከላከላል፣ ህገወጥነት፣ ተፈጽሞ ሲገኝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በህግ መሰረት ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል/ያስወስዳል 17.የልማት ቅደም ተከተል በማውጣት የማዕካልና የኮሪደር ቦታዎችን፡- ሀ. የማዕከላትና ኮሪደሮች ልማት የሚካሄድባቸውን ቦታዎች በፕላን ቅደም ተከተልና ህጉን መሰረት ያስለቅቃል፣ ለተነሺዎቹ በህግ መሰረት ካሳ ይከፍላል፣ ምትክ ቦታ ወይም ቤት ለሚያስፈለግቸው በህግ መሰረት ይሰጠቸዋል ፡፡ ለ. ከማንኛውም ህጋዊ የይገባኛል ጥያቄ ቦታዎቹ ነጻ በማስደረግ ለልማት ዝግጁ ያደርጋል፣ እንደ አግባቡ መሰረተ ልማት እንዲሟላ በማድረግ እንዲለማ ያደርጋል 18.በማዕካለትና በኮሪደሮች ውስጥ ሕጋዊ ባለይዞታዎች በልማቱ የሚሳተፉበት ስልት ቀይሶና አፈጻጸም አቅድ በማዘጋጀት ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን በዘርፉ በኩል ለቢሮ ስትራቴጅክ ካውንስል ያቀርበል ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ይህም ፡- - በግል ይዞታቸው በልማት አከባቢ በተዘጋጀው የከተማ ንድፍ ጥናት መሰረት ሊያስገነባ የሚያስችል ቦታ ስፋትና የማልማት አቅም (መመሪያ ቁጥር 79/ 2014) በተፈቀደ ጊዜ ገደብ ማልማት የሚችለትን - ኩታ ገጠም ይዞታቸወን በመቀላቀል በጋራ የአከባቢውን ዲዛይን ሊያስገነባ የሚችል ቦታ ስፋት እና የማልማት አቅም (በመመሪያ ቁጥር 79/ 2014) በተወሰነ ጊዜ ለማጠናቀቅ ውል ገብተው ቅድሚያ ማልማት የሚፈልጉ - በካሳና ምትክ መስተንግዶ መመሪያ ቁጥር 79/2014 የሚሰጠውቸው ምትክ ይዞታ ስፋት መጠን በጋራ ተደራጅቶ ለአከባቢው የከተማ ንድፍ ሊያስገነባ የሚያስችል የቦታ ስፋትና የማልማት አቅም በማረጋገጥ እንዲሰጥ የሚፈልጉትን - በካሳና ምትክ መስተንግዶ መመሪያ ቁጥር 79/ 2014 መሰረት ተሰልቶ የሚሰጠው ገንዘብ ልክ በልማት አካባቢ ከሚገነበው የመንግስት ቤት ምትክ እንዲሰጥ የሚፈልጉትን - በልማቱ ምክንያት ተነሺ የሆኑ እና ምንም ገቢ የሌላቸው ተነሺዎችን መልሶ የማቋቋሚበት እና የስራ ዕድል የሚያገኙበትን ሁኔታ 19.ለማዕከላትና ለኮሪደሮች ልማት ከተዘጋጁ ቦታዎች በዝርዝር ዲዛይን መሰረት በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የሚለሙ ቦታዎችን በቢሮ ፕሮሰስ ካውንስል ውይይት ከተደረገ በኃላ በከተማው ካቢኔ ሲጸድቅ ተግባራዊ እንዲደረግ ክትትል ያደርጋል ፡፡ 20. ለማዕከላትና ለኮሪደሮች ልማት ከተዘጋጁ ቦታዎች ውስጥ በግሉ ዘርፍ ሊለሙ የሚችሉ በጨረታና በምደባ ሊተላለፉ ሚገባቸውን ቦታዎች ከመሬት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ በመሆን ይለያል፣ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ያስደርጋል፣ 21.የከተማ መዋቅራዊ ፕላን እና ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላኖች መሰረት በማድረግና ፍትሃዊና ኢኮኖሚያዊ የመሬት ልማትና አቅርቦት እንዲሁም የከተማ ማደስ ጥናት ስራዎችን ያከናውናል፤ እንዲከናወን ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ 22.የአከባቢ ልማት ፕላን ባልጸደቀላቸውና ወይም በመዋቅራዊ ፕላን ዝርዝር መዋቅራ አፈጻጸም ሥርዓት ያልተቀመጠላት ቦታ በላይዞታዎች ግንባታ ፍቃድ ከመውሰደቸው በፊት የፕላንና ልማት ኮሚሽን በሚሰጠው የዲዛይን ሀሳብ በማድረግ የግንባታ ፍቃድ የሚፈቀድበት አሰራር እንዲኖር የሥራ ቅንጅት ይፈጥራል ወይም የአከባቢ ልማት ፕላን እስክያስጠና ግንባታዎች እንዳይካሄዱ በቅንጅት ይሰራል፣ 23.በማዕከላትና ኮርደር አከባቢ የልማት ፕላን የተዘጋጀላቸው ቦታዎች መልሶ ለማልማት በግሉ ዘርፍ ወይም በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በሽርክና የማልማት ፍለጎት ያጠናል፤አፈጻጸም ስልት ይቀይሳል 24. በማዕከላትና ኮርደር አከባቢ የልማት ፕላን የተዘጋጀላቸው ቦታዎች መልሶ ለማልማት በግሉ ዘርፍ ወይም በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በሽርክና እንዲላማ በተዘጋጀው የትግባራ ስልት መሰረት አንዲያለሙ ከለማ መሬት ማስተላለፍ ጋር በጋራ ክትትል ያደርጋል፤ 25.በማዕከላትና ኮርደር አከባቢ የልማት ፕላን የተዘጋጀላቸው ቦታዎች መልሶ ለማልማት በግሉ ዘርፍ ወይም በመንግስትና በግሉ ዘርፍ በሽርክና እንዲላማ በካቢኔ ውሳኔ የተሰጠው አልሚዎች በተጠናው የከተማ ንድፍ እና የልማት ቅደም ተከተል ዕቅድን የሊዝ ውል አካል ሆኖ እንደፈጽም ክትትል ያደርጋል፤ 26.በማእከላትና ኮሪደሮች ልማት አከባቢ የሚካሄዱ ልማቶች በተቀመጠላቸው ከተማ ንድፍና ፣ ቅደም ተከተልና ጊዜ ገደብ እንዲለሙ ድጋፍ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ 27.የማእከላትና ኮሪደር አከባቢ ልማት የዓለም አቀፍ እና አገር ተሞክሮዎችን ይወስዳል ፣ ያደራጀል በከተማው ነበራዊ ሁኔታ የሚፈጽመበት ስልት ይቀይሳል 28.በየደረጃው የአቅም ክፍተቶችን በመለየት ክፍተትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንዲሰጥ ያደርጋል 29.የሥራ አፈጻጸሙን ሪፖርት በየወቅቱ እያዘጋጀ ለዘርፉ ያቀርባል፣
የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት
መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ ታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!