ዳይሬክቶሬቶች

የመብት ፈጠራ ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

አቶ ግዛቸው ሙሉጌታ

image description

የመብት ፈጠራ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት ተጠሪነቱ ለመብት ፈጠራና የይዞታ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡- 1.ከቢሮውና ከዘርፉ ዕቅድ ጋር የተናበበ የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ አዘጋጅቶ ይመራል፣ ተፈጻሚነቱንም ይቆጣጠራል፣ 2.በስሩ ያሉ የመብት ፈጠራ ቡድኖች አመታዊ እቅዳቸውን እንዲያዘጋጁ ያስተባብራል፣ 3.በስሩ ተጠሪ ለሆኑ ቡድኖች ተፈላጊው የሠው ኃይል፣ የአደረጀጀትና የአሠራር ሠነዶችና ሌሎች መመሪያዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ ስራ ቆጥሮ ይሰጣል ይቀበላል፡፡ 4.የቡድን መሪዎችን በመምራት ባለሙያዎች እንዲበቁ፣ እንዲበረታቱ፣ በጋራ የመስራት ባህል እንዲዳብር ያስተባብራል፣ ያበቃል፡፡ 5.ተሻጋሪ ስራዎች በጋራ የሚሰሩበትን ቲም ቻርት በማዘጋጀት ከመሰል ዳይሬክቶሬቶች ጋር ይፈራረማል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፣ 6.የባለሙያ ክህሎትና አመለካከት ክፍተት የሚሞላ ሥልጠና እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ 7.የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት መወጣት ያስችለው ዘንድ ሥራውን በዕቅድ ይመራል፤ ለሥራው አፈፃፀም ሊሟሉ የሚገባቸውን የቢሮ መገልገያዎች እንዲማሉ ያደርጋል፡፡ 8.የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ያልተዘጋጀላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የግል ባለይዞታዎች፣ የአርሶ አደር ይዞታዎች፣ የቀበሌ ቤቶች፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶቸን፣ በመሬት ባንክ የገቡ ባዶ ቦታዎች፣ ለምለም ቦታዎች፣ ፓርኮች ወዘተ የሚጠናቀቅበትና የሚመራበትን ዕቅድና ስልት ይቀይሳል፣ ለአመራር ያቀርባል ሲፈቀድ በጥብቅ ዲስፕሊን ተግባራዊ እንዲሆን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ 9.የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ያቀረቡ ባለይዞታዎች ማህደር ከወረዳ እና ክ/ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተደራጅቶ እንዲመጣ ከተቀናጀ መሬት መረጃና ማህደር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ድጋፍና ክትትል ለማድረግ፡- - የድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ያዋቅራል፣ - ዝክረ-ተግባርና ቼክ-ሊስት እንዲዘጋጅ ያስተባብራል፣ የተዘጋጀውን አረጋግጦ ያቀርባል፣ - በተዘጋጀው የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር መሰረት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ጠያቂዎች ማህደር ከክ/ከተሞች ወደ ማዕከል ማህደር ክፍል ርክክብ እንዲደረግ ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ የሚያግጥሙ ችግሮችን ለይቶ ያቀርባል፡፡ 10.የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለሚዘጋጅላቸው ይዞታዎች የሰነድ እና የቴክኒክ ማጣራቶች በተቀመጠው አሰራርና መመሪያ መሰረት እየተከናወኑ ስለመሆኑ ይቆጣጠራል፣ 11.የመብት ፈጠራ ስራው ከመሬት ይዞታ ምዝገባ እና ማረጋገጥ ስራ ጋር የሚቀናጅበትን ስልት በጋር በማቀድ ይሰራል፣ ያስተባብራል፣ 12.በየክ/ከተሞችና ወረዳዎች የሚከናወነው የመብት ፈጠራ ስራ በመሬት ይዞታና ምዝገባ ኤጀንሲ የማረጋገጥ ስራ የተጀመረባቸውን ቀጠናዎች መሰረት በማድረግ በተቀናጀ አግባብ እንዲከናወን መረሃ-ግብር እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ በተለይ የመስክ ልኬት ስራው በተገቢው ሁኔታ እንዲመራ ከወረዳዎች ጋር ማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም (Telegram Group and Whatsup group) ስራው እንዲከናወን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ 13.ከመብት ፈጠራ ስራ ጋር በተያያዘ የጂ.አይ.ኤስና የሲ.አይ.ኤስ የመረጃ ልዩነት ያለባቸው በመብት ፈጠራ ቡድን እንዲጣሩ በማድረግ ያጸድቃል፣ 14.የጂ.አይ.ኤስ ሺፍቲንግ ችግር ያለባቸውንና ከመብት ፈጠራ ቡድን የሚቀርቡ ማስተካከያዎች ከቴክኒክ አኳያ በአግባቡ እንዲጣሩ በማድረግ የሚቀርበውን ማስተካከያ ያጸድቃል ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል መረጃው ለሚመለከታቸው አካላት ይልካል፣ 15.ከመብት ፈጠራ ስራዎች ጋር በተያያዘ የወጡ መመሪያዎች፤ ደንቦች፤ ማስፈጸሚያ ማኑዋሎች ላይ የሚያጋጥሙ የአፈጻጸም ችግሮችንና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በጥናት እንዲለይ ያደርጋል፣ የውሳኔ ሀሳብ በማዘጋጀት ያቀርባል፣ 16.የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎች ለተዘጋጀላቸው ለግል ባለይዞታዎች ክፍያ መፈጸሙን፣ በቤዝ ማፕ መወራረሱን እንደዚሁም በስራው ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች ስለሰሩት ስራ መፈረማቸውን በማረጋገጥ ካርታውን ያጸድቃል፣ 17.የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተዘጋጀላቸው ባለይዞታዎች እንዲሰራጭ በሲስተም መልዕክት ስለመተላለፉ ክትትል ያደርጋል፣ ለባለይዞታዎች ከተሰራጨ በኋላ ከየክ/ከተሞች ጋር የማህደር ርክክብ መደረጉን ይከታተላል ያስተባብራል፣ 18.የይዞታ ማረጋገጫ ከመስጠት ጋር በተያያዘ የመልካም አስተዳደር ችግር የሆኑና የህግ ማሻሻያ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በዝርዝር በማስጠናት ከውሳኔ ሀሳብ ጋር ያቀርባል፣ ክትትል ያደርጋል፣ 19.ከመብት ፈጠራ ስራ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ አቤቱታና ቅሬታ ተቀብሎ እንዲጣሩ ያደርጋል ምላሽ ይሰጣል፤ 20.የሥራ ሪፖርት ከቡድን መሪዎች ይቀበላል፣ የቡድን መሪዎችን የሥራ አፈፃፀም ብቃትና የሥነ-ምግባር አከባበር ይገመግማል፣ ያበረታታል፣ ያርማል፣ 21.የመብት ፈጠራ ስራው በከተማ አስተዳደሩ በጸደቀው ቴክኖሎጂ (ሲስተም) እንዲፈጸም ያስተባብራል፣ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ክትትል ያደርጋል፣ 22.በየደረጃው የተከናወኑ ስራዎች ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊና የሩብ ዓመት የሥራ ሪፖርት በማደራጀት ያቀርባል፡፡ 23.በሚቀመጠው አሰራር መሰረት በስሩ የሚገኙ ቡድን መሪዎችን ይመዝናል፣ የፈጻሚዎች ምዘና በቡድን መሪው በተገቢው ሁኔታ መፈጸሙን ይከታተል፣ አፈጻጸሙን ለሚመለተው ያቀርባል፡፡ 24.በዘርፍ ኃላፊ የሚሠጡትን ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎች ያከናውናል፣

የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት

መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ ታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!

በዳይሬክቶሬት ስር ያለው አገልግሎት፡-: