የይዞታ አገልግሎትና ማስተካከል ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
አቶ ሸምሰዲን ድልሰቦ
የይዞታ አገልግሎትና ማስተካከል ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት ተጠሪነቱ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡- 1.የዳይሬክቲሬቱን ዕቅድ ከጽ/ቤቱ ዕቅድ ጋር በማናበብ ያቅዳል፤ ከስሩ ላሉት ቡድኖች ያከፋፍላል፤ 2.ለስራው የሚያስፈልግ ግብዓት እና በጀት እንዲሟላ ያደርጋል /ያስደርጋል፤ 3.መብት ያልተፈጠረላቸው ይዞታዎችን እንዲጠናቀቁ የመብት ፈጠራ ስራውን ይመራል፣ ያስተባራል ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፤ 4.የመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ቅ/ጽ/ቤት የማረጋገጥ ስራ በጀመረባቸው ቀጠናዎች ውስጥ ከማህደር ርክክብ ጋር በተያያዘ በዳይሬክቶሬቱ ፕሮሰስ ካውንስል የሲ.አይ.ኤስ እና የጂ.አይ.ኤስ መረጃ ልዩነቶችን ከቡድን አስተባባሪዎች ጋር በመሆን በመወሰን ለማዕከል እንዲፀድቅ ይልካል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 5.ነባር የይዞታ አገልግሎት ለውጦችን አሰራርና መመሪያን ጠብቆ እንዲጣራ ያደርጋል፣ በማረጋገጥም የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤ 6.የመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ቅ/ጽ/ቤት የይዞታ ማረጋገጥ ስራ በሚያከናውንባቸው ቀጠናዎች የመረጃ ማስተካከያ ስራ እና በይዞታ ይካተትልኝ የሚዘጋጅ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በቴክኒክ ባለሙያ፣ በሰነድ አጣሪና በቡድን መሪው መጣራትና መረጋገጡን፣ በመሰረታዊ ካርታ መወራረሱንና ክፍያ መፈፀሙን አረጋግጦ ያፀድቃል፤ 7.ከመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ቅ/ጽ/ቤት የሚቀርብ የማህደር ርክክብ ጥያቄ እና የይዞታ ማስተካከያ የሚቀርብባቸውን ይዞታዎች በወቅቱ ምላሽ እንዲያገኙ በበላይነት ይመራል ያስተባብራል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 8.የሚሰጡ መደበኛ የየይዞታ አገልግሎቶች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ እና መመሪያ መሰረት እንዲሆን ይከታተላል ይደግፋል፤ 9.ዘርፉን ወክሎ በተለያየ ስልጠናዎች እና ስብሰባዎች ላይ ይሳተፋል፣ 10.ከፈፃሚዎች እና ከተገልጋዩ የሚቀርብለትን ጥቆማዎች፣ አስተያየቶች እና ቅሬታዎችን በመቀበል የስራ አፈፃፀሙን ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፤ 11.በዳይሬክቶሬቱ ስር ያሉ ቡድኖችን በበላይነት ይመራል ያስተባብራል፤ 12.በዳይሬክቶሬቱ ፕሮሰስ ካውንስል ደረጃ የሚወሰኑ ጉዳዮችን አይቶ ከአሰራርና መመሪያ አንፃር በጋራ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፣ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤ 13.ለዳይሬክቶሬቱ ለሚቀርቡና ውሳኔ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች የውሳኔ ሀሳብ በማቅረብ ያስወስናል፣ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል 14.በየደረጃው በአገልግሎት አሰጣጥ እና በአሰራር ችግር ለሚነሱ ቅሬታዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል፣ 15.በስሩ ያሉትን ቡድኖች አፈፃጸም በጋራ ይደግፋል፣ይመዝናል፣ ይገመግማል ለክፍለ ከተማው ጽ/ቤትና በቢሮ ደረጃ ለሚገኘው ዘርፍ በየጊዜው ሪፖርት ያደርጋል፤
የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት
መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ የታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!