ዳይሬክቶሬቶች

የተቀናጀ መሬት መረጃና ማህደር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

አቶ ዘሪሁን ቢቂላ

image description

የተቀናጀ መሬት መረጃ አያያዝና ማህደር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት ተጠሪነቱ ለአገልግሎት ማሻሻያና መሬት መረጃ ዘርፍ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል 1.የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ ከዘርፉ ጋር ተናባቢ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጅ ያደርጋል በስሩ ላሉ ቡድኖች/ባለሙያዎች በተናበበ መልኩ ያወርዳል አተገባበሩን ይመራል ይከታተላል፤ 2.ለዳይሬክቶሬቱ የተመደበውን በጀት እና ግብዓት በአግባቡ ስራ ላይ ያውላል/እንዲውል ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 3.የመሬት ይዞታ ማህደራትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ዲጂታይዝ በማድረግ እንዲጠበቅ ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 4.የመሬት መረጃ በቴክኖሎጂ የሚዘምንበትን ስርዓት በጥናት ይለያል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲለማ ያደርጋል ይተገብራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ 5.የመሬት መረጃዎች በመሰረታዊ ካርታ (base map) እንዲደራጅ ያደርጋል፣ መረጃዎችን በዳታ ቤዝ (data base) እንዲደራጅ ያደርጋል እና የጂ.አይ.ኤስ. መረጃ እርማት ወቅታዊ እንዲደረግ በማድረግ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ 6.ከተለያዩ ሴክተሮች የሚላኩ ልዩ ልዩ የፕላን ጥናቶች፣ ማሻሻያዎችና የጸደቁ ዲዛይኖችን እንዲደራጅ እና እንዲሰራጭ ያደርጋል፣ 7.በቢሮው በየደረጃው የሚሰጡ የመሬት አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እንዲሰጥ የአገልግሎት አሰጣጥ ማንዋሎችንና ስታንዳርዶችን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል ግብረ መልስ ይሰጣል፤ 8.ለምተው ተግባራዊ በሆኑ ቴክኖሎጂዎች ላይ በየደረጃው ለሚገኙት ባለሙያዎችና አመራሮች የአተገባበር ስልጠና ይሰጣል እንዲሰጥ ያስተባብራል፤ 9.የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጥ እና ለተገልጋዩ ተደራሽ የሆነ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የስራ ፍሰት ያዘጋጃል፣ ተፈጻሚ እንዲሆን ያደርጋል፣ ያስደርጋል፣ 10.አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጥ ሲስተም እንዲለማ ያደርጋል፣ ያስተዳድራል፣ 11.የተለያዩ የተቋሙ የህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች በድህረ ገጽ ለተገልጋዩ ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፣ 12.የተበላሹ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በራስ አቅም/በሌላ አካል እንዲጠገን ያደርጋል አዳዲስ ፕሮግራሞችን ወቅታዊ ያደርጋል፣ 13.በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ መረጃ አደረጃጀት፣ ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ እንዲሰጥ ያደርጋል አስተባብሮ ይመራል፣ 14.ቀደም ሲል ታትመው አገልግሎት የማይሰጡ ካርታዎችን በወቅቱ እንዲወገዱ ያስደርጋል አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ 15.በየደረጃው የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችንና የመረጃ ደህንነት እንዲረጋገጥ ክትትል ያደርጋል ፣ 16. የመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የማረጋገጥ ስራ በጀመረባቸው ቀጠናዎች ውስጥ ለርክክብ የተለዩ ማህደራት አስፈላጊ የሆኑ እና በሚመለከተው የስራ ክፍል የተለዩ የሰነድ ማስረጃዎች ስካን የማድረግ ስራ ያስተባብራል ይደግፋል፣ 17. ከዘርፍ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጨማሪ ስራዎች ያከናውናል፡፡

የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት

መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ ታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!