የቅሬታ አፈታት ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ዘቢደር ይፍሩ
የቅሬታ አፈታት ዳይሬክተር ተግባርና ኃላፊነት ተጠሪነቱ ለአገልግሎት ማሻሻያና መሬት መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡- 1.ከቢሮው ዕቅድ ጋር የተናበበ የቡድኑን ዕቅድ አዘጋጅቶ ይመራል፣ ተፈጻሚነቱንም ይቆጣጠራል፣ 2.ከክ/ከተሞች የህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ክትትል ቡድን ጋር በመቀናጀት ከቅሬታ እና መልካም አስተዳደር ስራዎች ጋር በተያያዘ ቅንጅት በመፍጠር ያቅዳል፣ ይሰራል፣ ያስተባብራል፣ ፣ 3.በሰሩ ተጠሪ ለሆኑ ፈጻሚዎች ተፈላጊው የሠው ኃይል፣ የአደረጀጀትና የአሠራር ሠነዶችና ሌሎች መመሪያዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ 4.ባለሙያዎች እንዲበቁ፣ እንዲበረታቱ፣ በጋራ የመስራት ባህል እንዲዳብር ያስተባብራል፣ ያበቃል፣ 5.ቡድኑ ከሌሎች የስራ ክፍሎች ጋር ሊኖረው የሚችለውን ትስስር በማጥናት የተጠናከረና ተመጋጋቢነት ያለዉ የሥራ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ይከታተላል፣ 6.የፈጻሚዎች ክህሎትና አመለካከት ክፍተት የሚሞላ ሥልጠና ይሰጣል፣ እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ 7.ለቡድኑ የተሰጠው ተግባር በተሟላ ሁኔታ እንዲፈጸም ክ/ከተሞችን የሚደግፍ የክትትልና ድጋፍ ኮሚቴ ያዋቅራል፣ ቼክ ሊስት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት ክትትልና ድጋፉን ያስተባብራል ግብረ-መልስ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ 8.ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ይለያል፣ በተናጥልና በቅንጅት እንዲፈቱ ክትትል ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን በመጠመር ያቀርባል፣ 9.ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ እንዲቀርብ ያደርጋል፣ ተፈጻሚነቱንም ይከታተላል፣ 10.ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተያያዘ ለቅሬታ ምንጭ የሆኑ አሰራሮችን በጥናት ይለያል፣ መፍትሄ እንዲሰጣቸው የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ 11.በስራ ላይ ያሉ መመሪያዎችንና የአሠራር ማኑዋሎች ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲለዩ ያስተባብራል፣ የህዝቡን ጥያቄዎች መመለስ በሚችሉበት ሁኔታ እንዲሻሻሉ ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ 12.በየደረጃው ከሚሰጡ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ይቀበላል፣ በስሩ ያሉ ባለሙያዎችን በማቀናጀት እንዲጣራ ያደርጋል፣ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ያረጋግጣል፣ ተቀባይነት ለሚያገኙት እንዲፈጸሙ ያስተባብራል፣ 13.አገልግሎት አሰጣጡ በቴክኖሎጂ እንዲፈጸም በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት ይፈጽማል፣ 14.ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊና የሩብ ዓመት የሥራ ሪፖርትን ያቀርባል፡፡ 15.በሚቀመጠው አሰራር መሰረት በስሩ የሚገኙ ባለሙያዎችን ይመዝናል፣ ለሚመለከተው ያቀርባል፡፡ 16.በዘርፍ ኃላፊ የሚሠጡትን ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን ያከናውናል፣
የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት
መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ ታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!
በዳይሬክቶሬት ስር ያለው አገልግሎት፡-:
ምንም አልተገኘም.