ህግና ቴክኒክ ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
አቶ ደረጀ ላቀው
የህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ክትትል ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት ተጠሪነቱ ለአገልግሎት ማሻሻያና መሬት መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡- 1. ከቢሮውና ከዘርፉ ዕቅድ ጋር የተናበበ የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ አዘጋጅቶ ይመራል፣ ተፈጻሚነቱንም ይቆጣጠራል፣ 2. የክ/ከተሞች የህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ክትትል ቡድኖች አመታዊ እቅዳቸውን እንዲያዘገጁ ያስተባብራል፣ 3. በሰሩ ተጠሪ ለሆኑ ቡድኖች ተፈላጊው የሠው ኃይል፣ የአደረጀጀትና የአሠራር ሠነዶችና ሌሎች መመሪያዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ ስራ ቆጥሮ ይሰጣል ይቀበላል፡፡ 4. የቡድን አስተባባሪዎችን በመምራት ባለሙያዎች እንዲበቁ፣ እንዲበረታቱ፣ በጋራ የመስራት ባህል እንዲዳብር ያስተባብራል፣ ያበቃል፡፡ 5. ተሻጋሪ ስራዎች በጋራ የሚሰሩበትን ቲም ቻርት በማዘጋጀት ከመሰል ዳይሬክቶሬቶች ጋር ይፈራረማል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፣ 6. የባለሙያ ክህሎትና አመለካከት ክፍተት የሚሞላ ሥልጠና እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ 7. የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት መወጣት ያስችለው ዘንድ ሥራውን በዕቅድ ይመራል፤ ለሥራው አፈፃፀም ሊሟሉ የሚገባቸውን የቢሮ መገልገያዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፡፡ 8. ክ/ከተሞችን የሚደግፍ የክትትል፣ ድጋፍ ቡድን ያዋቅራል፣ ቼክሊስት ያዘጋጃል፣ በተቀመጠው መርሀ-ግብር መሰረት ክትትልና ድጋፉን ያስተባብራል ሪፖርት እንዲዘጋጅ በማድረግ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ 9. ከፍ/ብሄር ክርክሮች ጋር በተያያዘ ከተለያዩ ፍርድ ቤቶች ለቢሮው የሚመጡ ወይም በጋራ የሚሰሩ፡- 10. የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ያላቸው ወይም 11. ካርታ ያልተሰጣቸው ባለይዞታዎች፣ 12. ከመሬት ባንክ፣ መሬት ማስተላለፍ፣ 13. ምትክ ቦታና ቤት፣ ከካሳ ክፍያ፣ ከአርሶ አደር ይዞታ እና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የመመሪያ፣ አሰራርና ቴክኒካል ጉዳዮች በአግባቡ እንዲሰጣሩ በማድረግ፣ ማስረጃ በማደራጀትና ማብራሪያ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ 14. ለፍርድ ቤት ትዕዛዞች መልስ ለመስጠት እንዲያስችል ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ተገቢውን የሰነድ ማስረጃ ያሰባስባል፣ ያደራጃል፣ 15. በፍርድ ቤት ትዕዛዙ መሰረት ከመመሪያ፣ አሰራር እና ቴክኒክ አኳያ ማስረጃ እንዲጣራ ያደርጋል፣ ከማህደር ሰነድ ያደራጃል ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት አግባብነት ያለው ምላሽ ይሰጣል፣ 16. ለፍርድ ቤት በሚሰጡ ምላሾች ላይ ከመመሪያ፣ አሰራር እና ቴክኒክ አኳያ ለሚቀርብ ተጨማሪ ትዕዛዝ በችሎት በመገኘት ማብራሪያ የሚሰጥ ባለሙያ ይመድባል፣ ይሰጣል፣ 17. በፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች ማለትም በፍርድ አፈጻጸም እንዲያስተገብር የሚቀርቡ ትዕዛዞችን ይቀበላል፣ በውሳኔው መሰረት እንዲፈጸም ባለሙያ ይመድባል፣ 18. ከፍ/ብሄር ክርክሮች ጋር በተያያዘ ለሚደረጉ የሰነድ ማጣራት ስራ ተገቢው ክፍያ መፈጸሙን ክትትል ያደርጋል፣ ይቆጣጠራል፣ 19. ቢሮው በሚከሰስበት ወቅት ውጤታማ ክርክር ለማድረግ እንዲያስችል፡- 20. የመስክ ልኬት እንዲከናወን፣ ልዩ ልዩ የሰነድ ማስረጃ እንዲሰበሰብ፣ ከመሰረታዊ እና መስመር ካርታዎች እንዲጣራ፣ ከልዩ ልዩ ፕላኖች አንጻር እንዲታይ/እንዲጣራ ያስተባብራል፣ 21. ማስረጃ እንዲደራጅ፣ ማብራሪያ/ምላሽ እንዲዘጋጅ በማድረግ ለፍትህ ቢሮ በደብዳቤ ይልካል፣ 22. ቢሮው በተከሰሰባቸው ጉዳዮች የባለሙያ ምስክርነት ሲያስፈልግ ባለሙያ ይመድባል፣ ምስክርነትም ይሰጣል፣ 23. ከፍትህ ቢሮ የሚመጡ የክስ/ ይግባኝ መጥሪያ ለተከሳሽ እንዲደርስ ከክ/ከተማ የህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ቡድን ጋር ይሰራል፣ 24. የወራሽነት ማጣሪያ ጥያቄዎች በትዕዛዙ መሰረት እንዲፈጸም ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች መረጃ በመጠየቅ በደብዳቤ ምላሽ ይሰጣል፣ 25. የፍትህ አካላት (ወንጀል ምርመር፣ ፖሊስ፣ ስነ-ምግባርና ጸረሙስና፣ ሌሎች ከወንጀል ጋር በተያያዘ የማጣራት ስራ የሚያከናውኑ አካላት) ለሚያቀርቧቸው ልዩ ልዩ የማስረጃና ማብራሪያ ጥያቄዎች መረጃ የማጣራትና የማደራጀት ስራዎችን ያስተባብራል፣ ምላሽም ይሰጣል፣ 26. የፍትህ አካላት (ወንጀል ምርመር፣ ፖሊስ፣ ስነ-ምግባርና ጸረሙስና፣ ሌሎች ከወንጀል ጋር በተያያዘ የማጣራት ስራ የሚያከናውኑ አካላት) ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ሙያዊ ዕገዛ የሚያደርጉ ባለሙያዎችን ይመድባል፤ 27. የፍትህ አካላት (የወንጀል ምርመራ፣ ፖሊስ …) ለሚያቀርቡት የቤት ወይም የህንጻ ግምት ጥያቄ በአግባቡ እንዲሰላ በማድረግ በደብዳቤ ምላሽ ይሰጣል፤ 28. የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ እንዲያግዝ ለባለሙያዎችና አመራሮች በአዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያዎችና የአፈጻጸም ማኑዋሎች ላይ የስልጠና ፍላጎት እንዲለይ በማድረግ ስልጠና ይሰጣል፣ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ 29. ስራ ላይ የዋሉ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ማስፈጸሚያ ማዋሎች እና አሰራሮች ላይ የሚያጋጥሙ የአፈጻጸም ችገሮችንና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ከሚለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን በጥናት እንዲለይ ያደርጋል፣ የውሳኔ ሀሳብ በማዘጋጀት ያቀርባል፤ 30. ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ የማብራሪያ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፣ ከህግ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ምክረ ሀሳብ ያቀርባል፣ 31. ዳይሬክቶሬቱ ከሚያከናውናቸው ስራዎች ጋር በተያያዘ የሚቀርብ አቤቱታና ቅሬታ ተቀብሎ እንዲጣሩ ያደርጋል፣ የውሳኔ ሀሳብ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ያረጋግጣል፣ ምላሽ ይሰጣል፤ 32. አገልግሎት አሰጣጡ በከተማ አስተዳደሩ በጸደቁ ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጸም ያስተባብራል፣ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ክትትል ያደርጋል፣ 33. የሥራ ሪፖርት ከቡድን አስተባባሪዎች ይቀበላል፣ የቡድን አስተባባሪዎችን የሥራ አፈፃፀም ብቃትና የሥነ-ምግባር አከባበር ይገመግማል፣ ያበረታታል፣ ያርማል፣ 34. በየደረጃው የተከናወኑ ስራዎች ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊና የሩብ ዓመት የሥራ ሪፖርት በማደራጀት ያቀርባል፡፡ 35. በሚቀመጠው አሰራር መሰረት በስሩ የሚገኙ ቡድን መሪዎችን ይመዝናል፣ የፈጻሚዎች ምዘና በቡድን መሪዎች በተገቢው ሁኔታ መፈጸሙን ይከታተል፣ ለሚመለከተው ያቀርባል፡፡ 36. በዘርፍ ኃላፊ የሚሠጡትን ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን ያከናውናል፣
የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት
መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ ታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!