ጽ/ቤት ኃላፊ
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
አቶ ኻሊድ ነስረዲን
ጽ/ቤት ኃላፊ
የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልእክት
መንግስት ያስቀመጠው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሬትን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መርቶ የታለመውን ውጤት እንደ ሀገር መጎናጽፍ የሚያስችል ነው ፡፡ይሁን እንጂ በፖሊሲው መሰረት በዘርፉ ያለውን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አረጋግጦ ታለመውን ውጤት ከማግኘት አንጻር የሚፈለገው ደረጃ ለመድረስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፡፡መሬት የህዝብና የመንግስት ውስንና ማይተካ ሀብት በተወሰኑ ግለሰቦችና እና ድርጅቶች ያለ አግባብ ለመበልጸግ ብልሹ አሰራርን የሙጥኝ የሚሉና የዘርፉን ልማት ወደ ኃላ የሚጎትቱ በመኖራቸው መሬትን በተገቢው አካል በተፈለገው ጊዜ ከማልማት አንጻር ውስንነቶች ይታይበታል፡፡ዘርፉን ስራ የሚመራውና የሚፈፅመው አካልም ቁርጠኛ ሆኖ ኃላፊነቱን አለመወጣቱና ለሌብነትና እና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመወጣቱ ሌላው ችግር ነው፡፡ እያንዳንዱን ቁራሽ መሬት ተገቢ ለሆነው ልማት ማዋል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ሁሉንም መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋሉ በተለይ የከተማን መሬት ዘመናዊ ፍትሐዊ አሰራርን ተከትሎ መምራትና ከታለመው ግብ ላይ ማድረስ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ለዘመናት ያለ ፕላንና በዘፈቀደ አሰፋፈር ዛሬ ላይ የደረሰችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እና ውብ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የነበረውን መጥፎ ስም ለመቀየርና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት በአዲስ መንፈስ መንቀሳቀስ ጀምረናል ፡፡አዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት መዲናነቷ እና የብዙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መቀመጫም በመሆን ታገለግላለች ፡፡ሰለሆነም ከተማዋን ዘመናዊ ደረጃዋን የጠበቀችና ተወዳዳሪ ለማድረግ መስራት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳዩ አይደለም ፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዘረፉ አመራሮች ፈጻሚዎች የሌብነት አስተሳሰብንና ተግባርን ብሎም ተገልጋይን የማጉላላት እጅ መንሻ መፈለግ አጸያፊ ባህሪን አስወግደው ተቋማችንንም ሆነ ከተማችንን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር እንዲፈጽሙ በአመለካከት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው፡፡ የየዘረፉ አመራሮች እስከ ታች ወርደው የክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብለን የለየናቸውን አሰራሮች እና መመሪያዎች ደረጃ በደረጃ እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ፡፡በተለይ አገልገሎት አሰጣጡን ከእጅ ንኪኪ ለማላቀቅ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ቢሮው ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የጀመረውና አጠናክሮ የሚቀጥለው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ኦንላይን አገልግሎት አሰጣጡን ዘላቂና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲደራጅ ሁሉም የዘርፉ አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ ርብርብ አድርጎ ግቡን እንዲመታ ማስቻል ነው ፡፡ በአጠቃላይ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የድርሻችንን ለመወጣት የጀመርነውን ቅንጅታዊ እርምጃዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ፡፡በዘርፉ የተሳለጠ ውጤታማነት ቀጣይ የሆነ ተልዕኮን መወጣት የሚቻለው አመራሩና ፈጸሚው ቁርጠኛ የአገልጋይነት መንፈስ ይዞ መስራት ሲችልና መተኪያ የሌለው የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡ ማገልገል ክብር ነው! በቅንነትና በታማኝነት ህዝብን ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ነው!!
በዳይሬክቶሬት ስር ያለው አገልግሎት፡-:
ምንም አልተገኘም.