ማስረጃ አሰጣጥ
የማስረጃ አሰጣጥና ክትትል ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት
ተጠሪነቱ ለህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ክትትል ዳይሬክተር ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡-
- ከዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ ጋር በተናበበ አግባብ የቡድኑን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ በስሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች ቆጥሮ ይሰጣል፣ ባለሙያዎች እንያዲቅዱ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን በቅርበት ይከታተላል፣
- በቡድኑ የሚሰጡ አገልግሎቶች በተቀመጠላቸው እስታንዳርድና ተገልጋዩን በሚያረካ ሁኔታ እንዲሰጡ ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣
- በስሩ ያሉ ባለሙያዎች እንዲበቁ፣ እንዲበረታቱ፣ በጋራ የመስራት ባህል እንዲዳብር ያስተባብራል፣
- የባለሙያ ክህሎትና አመለካከት ክፍተት የሚሞላ ሥልጠና እንዲሰጥ የስልጠና ፍላጎት ይለያል፣ ስልጠና እንዲሰጥ ጥያቄ ያቀርባል፣
- ለቡድኑ የሚስፈልገውን የስራ መገልገያ ቁሳቁሶች ይለያል እንዲሟላ ጥያቄ ያቀርባል፣ ለባለሙያዎች ያሰራጫል፣ ስራ ላይ ስለመዋሉ ይከታተላል፣
- በክ/ከተሞች ለሚደረግ ድጋፍና ክትትል ዕቅድና ቼክ ሊስት ያዘጋጃል፣ በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ የተዘጋጀውን ሪፖርት ጠምሮ ግብረ-መልስ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
- ከተለያዩ ፍርድ ቤቶች ለሚቀርቡ ትዕዛዞች ማለትም፡-
- የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ያላቸው ወይም
- ካርታ ያልተሰጣቸው ባለይዞታዎች፣
- ከመሬት ባንክ፣ ማስተላለፍ፣ ካሳ ክፍያ
- ከአርሶ አደር ይዞታዎች ጋር በተያያዘ፣
- ምትክ ቦታና ቤት እንዲሁም ሌሎች የፍ/ብሄር ክርክሮች ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ ልዩ ልዩ ትዕዛዞች የቡድኑን ባለሙያዎች በማስተባበር ማስረጃ ማጣራት እና እንደአስፈላጊነቱ የመስክ ልኬት በማድረግ ማብራሪያ ወይም ምላሽ ወይም ማስረጃ እንዲዘጋጅ ያስተባብራል፣ አረጋግጦ ያቀርባል፣
- በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር ወይም ሌሎች የፍትህ አካላት ለሚያቀርቡት የቤት ወይም የህንጻ ግምት ጥያቄ ተገቢውን የስሌት ቀመር በመጠቀም እንዲሰላ ያስተባብራል፣ አረጋግጦ ያቀርባል፣
- ለፍርድ ቤት በሚሰጡ ምላሾች ላይ ለሚቀርብ የባለሙያ ምስክርነት ትዕዛዝ ተገቢውን ባለሙያ ይመድባል፣ እንደ አስፈላጊነቱም በችሎት በመገኘት ያስረዳል፣
- ቡድኑ ከሚያከናውናቸው ስራዎች ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ቅሬታ የማጣራት ስራውን ያስተባብራል የተዘጋጀውን ምላሽ አረጋግጦ ያቀርባል፣
- ከተለያዩ ፍርድ ቤቶች ለሚቀርቡ ልዩ ልዩ ትዕዛዞች በከተማ አስተዳደሩ በጸደቁ ቴክኖሎጂዎች (ሲስተሞች) ይፈጽማል፣ እንዲፈጸም በቡድን ደረጃ ያስተባብራል፣
- ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊና የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሞችን በስሩ ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር ይገመግማል፣ ሪፖርትን ያቀርባል፣ ፡፡
- በሚቀመጠው አሰራር መሰረት በስሩ የሚገኙ ባለሙያዎችን ይመዝናል፣ ለዳይሬክተሩ ያቀርባል፣
- በዳይሬክተሩ የሚሠጡትን ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን ያከናውናል፣