የተቀናጀ መሬት መረጃ

የተቀናጀ መሬት መረጃ

የተቀናቀጀ የመሬት መረጃ አያያዝ ቡድን መሪ ተግባር እና ኃላፊነት

ተጠሪነቱ የተቀናጀ መሬት መረጃ አያያዝና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፤

  1. የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ መሰረት በማድረግ የቡድኑን እቅድ ያዘጋጃል፣ ለባለሙያ ያከፋፍላል፤
  2. የታቀዱት ተግባራት በዕቅዱ መሠረት መከናወናቸውን ክትትልና ግምገማ ያድርጋል፣ የስራ መመሪያ ይሰጣል፤
  3. የሥራ አፈፃፀም ውጤቶችን በመመዘን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
  4. የቡድኑ የስራ መገልገያ ግብአቶች  እንዲሟሉ  ያደርጋል፤
  5. የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ከባለሙያዎች ይቀበላል፣ ተግባራቶች በተቀመጠላቸው እስታንዳርድ መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፣ ወቅቱን ጠብቆ ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡
  6. የተሰሩ ሥራዎችን የአፈጻጸም ሪፖርት አዛጋጅቶ ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፡፡
  7. የመሬት መረጃ አያያዝ በቴክኖሎጂ የሚዘምንበትን ዘዴ ይለያል፡፡
  8. ጥናቱን ለማካሄድ የሚረዳ ዝክረ-ተግባር ያዘጋጃል ያጸድቃል፡፡
  9. የመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያዎችን(መጠይቅ፣ ቼክሊስት፣ የተለያዩ ቅፃቅጾች…) እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
  10. የመረጃ አያያዝ ፍላጎት አይነት (spatial and non-spatial) በመለየት ቅጾች ይለያል፡፡
  11. በተዘጋጀው መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ መሰረት መረጃ መሰብሰቡንና መደራጀቱን ያረጋግጣል፡፡
  12. የተሰበሰበውና የተደራጀው የመረጃ ትንተና ሥራ በትክክል መሰራቱን ክትትል ያደርጋል፡፡
  13. የተዘጋጀው የጥናት ረቂቅ ሰነድ በሚመለከታቸው ያስተቻል፣ የተሰጠውን ጠቃሚ አስተያየት በግብዓትነት እንዲካተቱ በማድረግ የሰነዱ አካል ያስደርጋል፤
  14. የመረጃ ማዋቅር (Data structure) ያዘጋጃል፤
  15. የተዘጋጀውን የጥናት ሰነድ እንዲጸድቅ ያደርጋል፤
  16. የጸደቀውን የጥናት ሰነድ ሲስተም ዲዛይን እንዲዘጋጅ ለሚመለከተው የሥራ ክፍል ያስተላልፋል፤
  17. መብት የተፈጠረላቸው ይዞታዎችን፣ የተሰጡ የይዞታ አገልግሎቶችን፣ በመሬት ባንክ የተመዘገቡ ቦታዎችን፣ ለአልሚዎች የተላለፉ ቦታዎችን፣ ለተነሺዎች የተላለፉ ምትክ ቦታዎች እና ካሳ የተከፈለበትን ይዞታ በመሰረታዊ ካርታ (base map) እንዲደራጅ ያደርጋል፡፡
  18. በተቋሙ የሚከናወኑ የአርባን ዲዛይን መረጃዎች፣ የመሬት ዝግጅት መረጃ፣ የካሳ ግመታና የምትክ አገልግሎት መረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደግፈው እና ተደራጅተው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ለቴክኖሎጂ ልማት ቡድን አደራጅቶ  ያቀርባል፡፡
  19. በመረጃ ቋት የሚደራጁ የተነሺዎች የካሳ ክፍያ፣ የተሰጠ ምትክ ቦታ፣ ምትክ ቤት፣ በተለያየ አግባብ የተላለፉ የሊዝ ይዞታዎች እና ሌሎች መሬት ነክ መረጃዎች መገለጫዎች ( Attribute ) እንዲለይ ያደርጋል፡፡
  20. በዳታ ቤዝ ለሚደራጁ የይዞታ መረጃዎችን ኮድ እንዲሰጥ ያስደርጋል፡፡
  21. መረጃዎችን በተዘጋጀ የመረጃ ቋት መመዝገባቸውን እና በየጊዜው ወቅታዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፡፡
  22. እርማት የተደረገባቸውን የጂ.አይ.ኤስ መረጃዎችን ተቀብሎ በተስተካከለው ማስረጃ መሰረት  ወቅታዊ ያደርጋል፣ መረጃዎች ለስራ ክፍሎች እንዲሰራጭ ያደርጋል፡፡
  23. ከከተማ ፕላን ልማት ኮሚሽን ተሻሽለው የሚመጡ ልዩ ልዩ የፕላን ጥናቶችን መዝግቦ ይቀበላል፡፡
  24. ከከተማ ፕላን ልማት ኮሚሽን  ተሻሽለው የሚመጡ ልዩ ልዩ የፕላን ጥናቶችን በመሰረታዊ ካርታ (base map) እንዲደራጅ ያደርጋል፡፡
  25. ከከተማ ፕላን ልማት ኮሚሽን የሚላኩ ልዩ ልዩ የፕላን ጥናቶችን ለየስራ ክፍሉ ያሰራጫል፡፡
  26. ከመሰረተ ልማት ዘርጊ ተቋማት ለከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን እንዲጸድቁ የተላኩ ዲዛይኖችን ጸድቀው ሲመጡ እንዲመዘገቡ ያደርጋል፡፡
  27. በከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን የጸደቁ ዲዛይኖችን በመሰረታዊ ካርታ እንዲደራጅ ያደርጋል እንዲሁም ለስራ ክፍሎች እንዲሰራጭ ያደርጋል
  28. የተጠኑ የመረጃ አያያዝ እና አደረጃጀት ዘዴዎችን ተግባራዊ እንዲደረጉ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
  29. አጠቃላይ መረጃዎችን በተዋረድ ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ በየጊዜው ወቅታዊ መደረጋቸውን፣ መደራጀታቸውንና መሰራጨታቸውን ይከታተላል፣ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  30. ክትትልና ድጋፍ ተደርጎ ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲያገኙ ያሳውቃል አፈፃፀሙን ይከታተላል ያረጋግጣል፤
  31. የሥልጠና ፍላጎት እና የስልጠና ዓይነት ይለያል፡፡
  32. ሥልጠናው በራስ አቅምና በውጭ የሚሰጥ መሆኑን በመለየት ዝክረ ተግባር አዘጋጅቶ እንዲጸድቅ ለኃላፊ ያቀርባል፤
  33. ለሥልጠና የሚረዳ ሰነድ ያዘጋጃል፣ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
  34. በወጣው መርሀ-ግብር መሰረት ሥልጠና መሰጠቱን ክትትል በማድረግ አፈፃፀሙን በሪፖርት አዘጋጅቶ ለኃላፊ ያቀርባል፡፡
  35. ሌሎች ከሥራ ክፍሉ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን በበላይ ኃላፊ ሲመራለት ያከናውናል፣