የሶፍትዌር ልማት እና ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት

የሶፍትዌር ልማት እና ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት

የሶፍትዌር ልማት እና ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት

ተጠሪነቱ የተቀናጀ መሬት መረጃ አያያዝና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-

  1. የቡድኑን ዕቅድ ከዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ ጋር ተናባቢ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጅ ያደርጋል በስሩ ላሉ ባለሙያዎች በተናበበ መልኩ ያወርዳል አተገባበሩን ይመራል ይከታተላል፤
  2. ለቡድኑ የተመደበውን ግብዓት በአግባቡ ስራ ላይ ያውላል/እንዲውል ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  3. የመሬት መረጃ በቴክኖሎጂ የሚዘምንበትን ስርዓት በጥናት ይለያል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲለማ ያደርጋል ይተገብራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  4. በቢሮው በየደረጃው የሚሰጡ የመሬት አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እንዲሰጥ የአገልግሎት አሰጣጥ ማንዋሎችንና ስታንዳርዶችን ያዘጋጃል ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል አፈፃፀሙን ይከታተላል ግብረ መልስ ይሰጣል፤
  5. ለምተው ተግባራዊ በሆኑ ቴክኖሎጂዎች ላይ የአተገባበር ስልጠና ይሰጣል ያሰጣል፤
  6. የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጥ እና ለተገልጋዩ ተደራሽ የሆነ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የስራ ፍሰት ያዘጋጃል፣ተፈጻሚ እንዲሆን ያደረግጋል፣/ያስደርጋል፣
  7. ሲስተም እንዲለማ ያደርጋል፤
  8. የተለያዩ የተቋሙ የህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች በድህረ ገጽ ለተገልጋዩ ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል
  9. የተበላሹ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በራስ አቅም/በሌላ አካል እንዲጠገን ያደርጋል አዳዲስ ፕሮግራሞችን ወቅታዊ እንዲደረግ ያደርጋል፤
  10. በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ መረጃ አደረጃጀት፣ ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ እንዲሰጥ ያደርጋል አስተባብሮ ይመራል
  11. በየደረጃው የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችንና የመረጃ ደህንነት እንዲረጋገጥ ክትትል ያደርጋል ፣
  12. የገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ የሚዘምንበት ስርዓት ማጥናትና ማልማት /እንዲለማ ያደርጋል
  13. ሲስተም የማስተዳደር ስራን ይመራል ያስተባብራል፤
  14. ዌብ የማስተዳደር ስራን ይመራል ያስተባብራል
  15. የተቀናጀ የመሬት መረጃ የሚደራጅበት ሶፍትዌር ማበልፀግ/እንዲበለጽግ ማስደረግ
  16. የመረጃ ቋት የማስተዳደር ሥራ ይመራል ያስተባብራል፤
  17. የኔትዎርክ መሰረተ ልማት ይለያል፣ እንዲዘረጋ ማድረግና ያስተዳድራል
  18. የመረጃ ደህንነት እንንዲጠበቅ ያደርጋል
  19. የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ያደርጋል በጥናቱ መሰረት በስራ ክፍሉ ባሉ ባለሙያዎች ዝክረ ተግባር እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣በተዘጋጀው ዝክረ ተግባር መሰረት ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል
  20. በተቋሙ ውስጥ ያሉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን መጠገን እንዲጠገን ማድረግ
  21. ከላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያሳውቃል፣
  22. ከሌሎች ሥራ ክፍሉ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን በበላይ ኃላፊ ሲመራለት ያከናውናል
  23. የስራ አፈጻጸም ይመዝናል፤ይገመግማል፤ክፍተቶችን ይለያል፤የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ አማራጮችንም በመለየት ተግባራዊ ያደርጋል፤