የሪከርድና የተገልጋይ መስተንግዶ

የሪከርድና የተገልጋይ መስተንግዶ

​​​​​​የተገልጋይ መስተንግዶና ሪከርድ ቡድን መሪ

ተጠሪነቱ ለተቀናጀ መሬት መረጃና ማህደር አስተዳደር ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፤

  1. የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የራሱን ዕቅድ ያዘጋጃል፣
  2. ደብዳቤዎችን እና መረጃዎችን በመረከብ ማህተም፣ ቀን፣ ቁጥርና አባሪ መኖሩን በማረጋገጥ በገቢ ካርድ እንዲመዘገብ ያደርጋል፣
  3. የገቢ ካርድ የተመዘገቡ ደብዳቤዎችንና መረጃዎችን ከሚመለከተው ፋይል ጋር በማያያዝ ቁጥር በመስጠት ለሚመለከተው አካል መተላለፉን ይከታተላል ያስተባብራል፤
  4. ፋይሉ ጉዳዩ አልቆ ሲመለስ በማህደሩ ውስጥ ያሉ ገጾችን በጥንቃቄ ቆጥሮ ይረከባል ፣ ለደብዳቤዎች መልስ የተሰጣቸው መሆኑን ያረጋግጣል ፣ ይከታተላል ያስተባብራል ፣ 
  5. ወደተለያዩ ተቋማት ወይም መ/ቤቶች የሚላኩ ወይም የሚወጡ ደብዳቤዎችን በትክክለኛው መፈረሙን ያረጋግጣል፤ይከታተላል፤ያስተባብራል
  6. ወጪ የሚደረጉ ደብዳቤዎችን ትክክለኛነት ካጣራ በኋላ የፕሮቶኮል ቁጥር በመስጠት ወጪ እንዲሆኑ ወደ ሚመለከተው ክፍል መላኩን ይከታተላል ያስተባብራል፤
  7. ደብዳቤዎች ወጪ ከተደረጉ በኋላ ቀሪ ደብዳቤዎች ከማህደር ጋር ተያይዘው በተገቢው እና በተደራጀ መልኩ እንዲቀመጥ ያስደርጋል
  8. ገቢና ወጪ የተደረጉ ደብዳቤች፣መረጃዎችንና ማህደሮችን ዕለታዊ እንቅስቃሴ ይመዘግባል፣ ስታትስቲካል መረጃዎችን ሪፖርት ያደርጋል፤
  9. መ/ቤቱ በሚሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚመጡ ባለጉዳዮችን በአግባቡ በመቀበል የሚጠይቁትን መረጃና ማብራሪያ ይሰጣል፣ በራሱ የማይመለሱ ጥያቄዎች ከሆኑ የእንግዳ መግቢያ ካርድ በመስጠት ወደ ሚመለከተው ክፍል ያስተላልፋል፣
  10. የባለጉዳዮች አገልግሎት የማግኘት መብቶች፣ ለአገልግሎት አሰጣጡ ብቁ የሚያደርጉና መሟላት ያለባቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች መረጃዎችን መሰጠታቸውን ያስተባብራል፣ይከታተላል፤
  11. ለባለጉዳዮች እንዲሰጡ የሚዘጋጁ የጽሁፍ መረጃዎችን በአግባቡና በበቂ ብዛት አደራጅቶ በመያዝ ሲጠየቅ ይሰጣል፣እንዲሰጥ ያደርጋል፤
  12. በተገልጋዮች ፍላጎት መሰረት ቀልጣፋ የመረጃ አገልግሎት በመስጠት ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲያገኙ ቅድመ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እገዛ ያደርጋል፣
  13. በቢሮው በሚሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚመጡ ባለጉዳዮችን በአግባቡ በመቀበል የሚፈልጉትን የመረጃ/ የአገልግሎት አይነት ይጠይቃል፤ይሰጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል፤
  14. ከላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያሳውቃል፣ የባለሙያዎች የስራ አፈፃፀም ምዘና ያከናውናል ሪፖርት ያደርጋል፤
  15. ሌሎች ከሥራ ክፍሉ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን በበላይ ኃላፊ ሲመራለት ያከናውናል፤