የለማ መሬት ማስተላለፍ
የለማ መሬት ማስተላለፍ ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት
ተጠሪነቱ ለለማ መሬት ማስተላለፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤
- የቡድኑን እቅድ በማዘጋጃት ከዳይረክቶሬቱ ዕቅድ ጋር እንዲናበብ ያደርጋል፤
- የጸደቀውን የቡድኑን ዕቅድ በስሩ ላሉ ባለሙያዎች አቅርቦ የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ ዕቅዱን ለባለሙያዎች ያከፋፍላል፤
- የስራ መመሪያና አቅጣጫ በመስጠት የቡድኑን ሥራ ይመራል፣ ያስተባብራል፤
- ክፍሉን ወክሎ የጨረታ ኮሚቴው ፀኃፊ በመሆን ያገለግላል፤
- ለሥራ ክፍሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንዲሟሉለት ይከታተላል፤
- የቡድኑን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ከዳይሬክቶሬቱ ጋር የግምገማ መድረኮች ያዘጋጃል፣ይመራል፣ በአፈጻጸም ላይ የታዩ ችግሮችን ይለያል የመፍትሄ ሀሳቦችን ያዘጋጃል፤
- በሥሩ ለሚገኙ ባለሙዎች ያሉባችውን የአፈፃፀም ክፍተቶች እንዲለዩ በማድረግ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ያመቻቻል እንዲሁም ባለሙያዎች ያለባቸውን ክፍተት እርስ በእርስ እንዲሞሉ ያስተባብራል፤
- ከከንቲባ ጽ/ቤት ወይም ከመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተመራውን የመሬት ጥያቄ ይቀበላል ፣መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በሊዝ አዋጅ 721/2004 መሰረት መሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
- የአልሚው ጥያቄ ቅድመ ሆኔታዎችን ያሟላ ከሆነ ለመሬት ዝግጅት ደብዳቤ እንዲዘጋጅ ይመራል፤
- ለመሬት ዝግጅት የተዘጋጀው ደብዳቤ በሕግ ማቀፍ መሰረት የተዘጋጀ መሆኑን በማረጋገጥ ለኃላፊ ያቀርባል፤
- በካሳና ምትክ፣ በመሬት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጅውን መሬት በሃርድ እና በሶፍት ኮፒ ተቀብሎ የተነሺዎችን ሰነድ ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ በአግባቡ መደራጅቱን ያረጋግጣል፤
- ለተገቢው ልማት እንዲውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን ባለው የሕግ ማቀፍና መዋቅራዊ ፕላን የውሳኔ ሀሳብ እንዲዘጋጅ ይመራል፡፡ የውሳኔ ሀሳቦዎች በሕግ ማቀፍና በመዋቅራዊ ፕላን መዘጋጅታቸውን ያረጋግጣል፤
- የተዘጋጀው የውሳኔ ሀሳብ ለከተማው አስተዳደር ካቢኔ ከመቅርቡ በፊት ከዘርፍና ዳይሪክቶሬት ኃላፊ ጋር ውይይት ያደርጋል፤
- በዘርፍ ደረጃ የፀደቀውን ውሳኔ እንዲስጥበት ለከተማ አስተዳደር ካቢኔ ወይም ለመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስትራጂክ ካውንስል እንዲቀርብ ያስደርጋል፤
- በከተማው አስተዳደር ካቢኔ ወይም በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል ወይም በዘርፍ ፕሮሰስ ካውንስል ውሳኔን መነሻ በማድርግ አልሚው ማሟላት ያለበትን ቅድመ ክፍያ እንዲሰላ በማድርግ ሊዝ ለሚያዋውለው የስራ ክፍል ያስተላልፋል፤
- በጨረታ የሚተላለፉ ቦታዎችን ከሚመለከተዉ አካል በወቅቱ ቦታዎቹ ተዘጋጅተው መምጣታቸውን ያረጋግጣል ፤ተዘጋጅተው የመጡት ቦታዎች ከማንኛውም የይገባኛል ክርክር ነጻ መሆናቸውን፣ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው መሆኑን፣ ለእያንዳንዱ ፕሎት የወሰን ችካል የተቸከለለት እና የጸዳ መሆኑን ለጨረታ ከመውጣታቸው በፊት ባለሙያዎችን በማስተባበር በመስክ እንዲረጋገጥ ያስደርጋል፤
- ከማንኛውም የይገባኛል ክርክር ነጻ የሆኑ፣ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ቦታዎችን በቪዲዮ ካሜራ እንዲቀረጽ ያስደርጋል፤
- በዘርፉ ፕሮሰስ ካውንስል የጸደቀውን የተጫራቾች መመሪያ፣የመልስ ማቅረቢያ ቅጽ፣ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎችን ፕላን ፎርማት ተለይተው እንዲዘጋጁ ያስደርጋል፤
- በጨረታ የሚተላለፉ ቦታዎችን ቦታው የሚገኝበት አድራሻ፣ ለጨረታ የወጡት ቦታዎች የሚጎበኙበት ቀን፣ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃበት ቀን፣ ጨረታው የሚዘጋበት ሠዓት፣ የማልማት አቅም ማሳያ፣የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን፣የቦታው አገልግሎት፣በቦታ ደረጃና በመነሻ ዋጋ እንዲለዩ ያስደርጋል፤
- በጨረታ የሚተላለፉት ቦታዎችን በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች/በቴሌቪዥን፣በኤፍ ኤም ሬድዮ፣ በጋዜጣ፣በተቋሙ በዌብ ሳይት/ እንዲለቀቅ ያስደርጋል፤
- በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን የተላለፈውን ማስታወቂያ ለተጨራቾች ግልጽ በሆነ መልኩ በተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መለጠፉን ክትትል ያደርጋል፤
- ለጨረታ የወጡት ቦታዎች በጋዜጣ በወጣው ፕሮግራም መሠረት ቦታዎቹ የሚገኙባቸው የክፍለ ከተማ ባለሙያዎች እንዲያስጎበኙ የቦታዎቹን ዝርዝር በሶፍትና በሀርድ ኮፒ በመላክ በመስክ እንዲጎበኙ ያስልካል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- ለጨረታ የተዘጋጁት ሰነዶች ሊቀርብ የሚችለውን ተጫራች ታሳቢ በማድረግ እንዲባዛ ያስደርጋል የሰነድ ሽያጭ ሂደቱ በአግባቡ ስለመከናወኑ ክትትል ያደርጋል ፤
- በተጫራቾች መመሪያ እና በማስታወቂያው በተቀመጠው መስፈርት መሠረት ተጫራቹ በተዘጋጀው የጨረታ መልስ ማስገቢያ ሣጥን ውስጥ እንዲያስገባ ባለሙያዎችን በመመደብ ማብራሪያና ገለጻ ይሰጣል ክትትል ያደርጋል፤
- ለጨረታ የወጣውን የፕሎት (የቦታ) ብዛት እና የተሸጠ የጨረታ ሰነድ ብዛትን ታሳቢ በማድረግ ጨረታው ለተጫራቾች በይፋ እየተበሰረ የሚቆይበትን ቀናት ከዳይረክቶሬቱ ጋር በመሆን ይወስናል በእየለቱ የጨረታውን ሂደት ይከታተላል፣ያስተባብራል፤
- በጨረታው ሂደት ቅሬታ ያለው ተጫራች የጽሁፍ ቅሬታን በመቀበል ለጨረታ ኮሚቴው በማቅረብ ምላሽ እንዲሰጥ ያስደርጋል፤
- በስትራቴጂክ ካውንስል የጸደቀውን የጨረታ አሸናፊዎች (1ኛ እና 2ኛ) የወጡትን ዝርዝር በመቀበል ያሸነፉበት ዋጋ፣ቅድመ ክፍያ፣ያሸነፉበት የቦታ ኮድ እና የቦታው አድራሻ እንዲሁም የሊዝ ውል የሚዋዋሉበት የጊዜ ገደብ ተገልጾ ለህትመት እንዲላክ መረጃውን እንዲደራጅ ያስደርጋል፤
- በጋዜጣ የወጣውን የአሸናፊዎች ዝርዝር መረጃ፣የጸደቀው ቃለ ጉባኤ፣ አሸናፊ ያገኙት ቦታዎች ፕላን ፎርማት በሶፍትና በሀርድ ኮፒ፣የጨረታ አሸናፊዎች ያስገቡት ሰነድ በማያያዝ የሊዝ ውል እንዲዋዋሉ አንዲተላለፍ ያደርጋል፤
- የጨረታ ተሸናፊዎችን ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በማደራጀት ተመላሸ ያስደርጋል፤
- የጨረታ አሸናፊዎች በተሰጠው የጊዜ ገደብ መሠረት የሊዝ ተዋውለው ቦታውን ስለመረከባቸው በሥሩ ባሉ ባለሙያዎች ክትትል ያስደርጋል ሂደቱን ይከታተላል፤
- አሸናፊዎች ቅድመ ክፍያ ከፍለው የሊዝ ውል ካልፈጸሙ ያሸነፉበትን ቦታ ወደ መሬት ባንክ ገቢ እንዲደረግ መረጃውን አደራጅቶ ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፤
- የቦታ ደረጃ፣ የሊዝ መነሻ ዋጋ እና ወቅታዊ አማካይ የጨረታ ዋጋ የጥናት መርሃ- ግብር በማዘጋጅት ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ያጸድቃል፤
- መረጃ እንዲሰበሰብ እና እንዲተነተን ያደርጋል፤
- የመስክ ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ በማስደረግ የተገኘውን ነባራዊ ሁኔታ ካለው የቦታ ደረጃ ካርታ ጋር የማገናዘብ ሥራ ያሰራል፤
- ነባራዊ ሁኔታውን ካለው የቦታ ደረጃ ካርታ ጋር በማናበብ የሊዝ መነሻ ዋጋ፣ አማካይ የጨረታ ዋጋ በተከታታይ ለሶስት ዙር ጨረታ ውጥቶባቸው አሸናፊ የተገኘባቸው ዝርዝር መረጃ መነሻ በማድረግ እንዲዘጋጅ ያስደርጋል፤
- የተጠናው የቦታ ደረጃ ፣ የሊዝ መነሻ ዋጋ እና ወቅታዊ አማካይ ጨረታ ዋጋ ሰነድ ለካቢኔ ከመቅርቡ በፊት በዘርፉና በዳይሪክቶሬቱ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደርጋል፤
- የተጠናው ጥናት የውሳኔ ሀሳብ ለካቤኔ እንዲቀርብ ያስደርጋል፤
- የተጠናው የቦታ ደረጃ፣ የሊዝ መነሻ ዋጋ እና ወቅታዊ አማካይ የጨረታ ዋጋ ጥናት ጸድቆ ሲመጣ ለክፍለ ከተማና ለሚመለከተው አካል እንዲያውቀው ያስደርጋል፤
- ሥራዎች በሊዝ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያዎችና የአሠራር ማንዋሎች መሠረት እየተፈጸሙ ስለመሆኑ ይከታተላል፤
- የአፈጻጸም መመሪያዎችና የአሠራር ማኑዋሎች በሥራ ላይ ሲዉሉ በባለሙያዎች የተለዩ ክፍተቶችን እና የቀረቡ የመፍትሄ ሀሳቦችን ያደራጃል፣ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ለዳይሬክቶሬቱ አደራጅቶ ያቀርባል፤
- በሥሩ ላሉ ባለሙያዎች የክህሎት ክፍተት በመለየት ስልጠናዎች እንዲሰጡ ለዳይረክቶሬቱ ያቀርባል፤
- በሥራ ላይ ያሉ አዋጅ፣ደንብና መመሪያዎችን አስመልክቶ ከሌሎች ዳይረክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች ጋር በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ እንዲመቻች ያስደርጋል፣ተሳታፊም ይሆናል፤
- ከውይይት መድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን በመዉሰድ ለቀጣይ ሥራ እንዲያመች በተቋሙ አመራሮች ዉሳኔ እንዲያገኝ አደራጅቶ ያቀርባል፤
- የድጋፍና ክትትል ዝክረተግባር ቼክ-ሊስት እና የመረካከቢያ ቅጽ ያዘጋጃል፣ተጫራቾች የሊዝ ውል በሚዋዋሉበት ወቅት ለክ/ከተሞች ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ችግሮች ካሉ በመለየት አደራጅቶ አቅጣጫ እንዲሰጥባቸው ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፡ ግብረ-መልስ ለክ/ከተሞች እንዲሰጥ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያሳውቃል፣
- ሌሎች ከሥራ ክፍሉ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን በበላይ ኃላፊ ሲመራለት ያከናውናል
- የስራ አፈጻጸም ይመዝናል፤ይገመግማል፤ክፍተቶችን ይለያል፤የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ አማራጮችንም በመለየት ተግባራዊ ያደርጋል፤