ሊዝ አፈፃፀም ክትትል

ሊዝ አፈፃፀም ክትትል

የሊዝ አፈጻጸምና ክትትል ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት​​​​​​​

ተጠሪነቱ ለለማ መሬት ማስተላለፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል

  1. ከዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ በመነሳት የቡድኑን ዕቅድ በወቅቱ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ ሲፀድቅም ስራዎችን ለባለሙያዎች በማከፋፍል ተግባራዊ ያደርጋል፤
  2. የቡድኑ ባለሙያዎች አመታዊ ወርሃዊ እና ሳምንታዊ እቅድ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፤
  3. የቡደኑ ባለሙያዎች በእቅዱ መሰረት በየሳምንቱ ያከናውኑትን ተግባራት ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይከታተል፤
  4. በቡድኑ የሚገኙ ባለሙያዎችን ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር እና ዉጤታማነታቸው እንዲጎለብት በቅርበት ይደግፋል፤
  5. አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ መሳሪያዎችና የሰው ሀይል እንዲሟላ ያስደርጋል፣ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ ይሰጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል፤
  6. ቡድኑ ለተገልጋዮች የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በአግባቡ መሰጠታቸውን እና ቅሬታም እንዳይከሰት ይከታተላል፣ ቅሬታ ሲፈጠር ማስተካከያ ይሰጣል፤
  7. እያንዳንዱ በቡድኑ ሥር ያሉ ባለሙያዎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ተግባራትን ማከናወናቸውን ይከታተላል ይደግፋል፤
  8. ከቢሮ ወይም ከክፍለ ከተማ የተላከውን እና  የተመራውን የሊዝ ውል ማሻሻያ ጥያቄ ይቀበላል፣
  9. ጥያቄው ተገቢ መሆኑን እንዲጣራ እና እንዲረጋገጥ ግንባታው ያለበትን ደረጃ በመስክ በባለሙያ እንዲረጋገጥ ያስደርጋል፤
  10. የግንባታውን ሪፖርትና አልሚው ያቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግ በሕግ ማዕቀፍና በከተማው መዋቅራዊ ፕላን መሠረት የውሳኔ ሃሳብ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
  11. የተዘጋጅው የውሳኔ ሃሳብ ባሉት የህግ ማዕቀፍ መሠረት የተዘጋጀ መሆኑን በማረጋገጥ ለዳይሬክተር/ለዘርፍ ለፕሮሰስ ካውንስል እንዲቀርብ ያደርጋል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቀርቦ ያስረዳል፤
  12. የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ተቀባይነት ካገኘ አልሚው ማሟላት ያለበትን መረጃ እንዲያሟላ በማድረግ የሊዝ ውል እንዲሻሻል ይመራል፤
  13. በሕግ ማዕቀፎች መሠረት ተዘጋጅቶ የመጣውን የሊዝ ውል መዘጋጀቱን በማረጋገጥ የሊዝ ውል ሰጪና የሊዝ ውል ተቀባይ ማጽደቃቸውን ያረጋግጣል፤
  14. የጸደቀውን የሊዝ ውል ማሻሻያ እና ሌሎች ሰነዶች እንዲደራጁ በማስደረግ ለክ/ከተማ ያስልካል፤
  15. ከቢሮ ወይም ከክፍለ ከተማ የተመራለትን/የተላከውን የአገልግሎት ለውጥ የሊዝ ውል ማሻሻያ ጥያቄው በሕግ ማዕቀፍ ምላሽ የሚያገኝ መሆኑን በማረጋገጥ የግንባታው ደረጃ እና በአሁኑ ሰዓት ቦታው እየሰጠ ያለው አገልግሎት በመስክ ተረጋግጦ እንዲቀርብ ለባለሙያ ይመራል፤
  16. የቀረበው የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄ የዋጋ ለውጥ ካለው ወይም በቦታው ላይ ህገወጥ ተግባራት ተፈጽሞ ከሆነ በሕግ ማዕቀፍና የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን መነሻ በማድረግ የውሳኔ ሃሳብ እንዲዘጋጅ ያስደርጋል፤
  17. የተዘጋጅው የውሳኔ ሃሳብ ለቢሮ ፕሮሰስ ካውንስል እንዲቀርብ ያስደርጋል እንደ አስፈላጊነቱ በአስረጂነት በመቅረብ ያስረዳል፤
  18. በቢሮ ፕሮሰስ ካውንስል የጸደቀው የውሳኔ ሃሳብ ተግባራዊ እንዲሆን የክፍያ ለውጥ ካለው ክፍያ እንዲፈጸም ያስደርጋል፤
  19. የተዘጋጀውን የአገልግሎት ለውጥ የሊዝ ውል ማሻሻያ ውል ሰጪና ውል ተቀባይ ማጽደቃቸውን ያረጋግጣል፤
  20. የፀደቀውን የሊዝ ውልና ሌሎች ሰነዶዎች በማደራጀት ለክፍለ ከተማ ያስልካ፤፡
  21. ከቢሮ ወይም ከክፍለ ከተማ ተመርቶ የመጣውን የፕሮግራም ለውጥ የሊዝ ውል ማሻሻያ ጥያቄ በሕግ ማዕቀፍ ምላሻ የሚያገኝ መሆኑን በማገናዘብ በመስክ የግንባታው ደረጃ እንዲረጋገጥ ለባለሙያ ይመራል፤
  22. የፕሮግራም ለውጥ የተጠየቀበት ቦታ ከሪል እስቴት መመሪያ ውጪ ግንባታ የተከናወነበት ከሆነ የውሳኔ ሃሳብ ለቢሮ ፕሮሰስ ካውንስል እንዲቀርብ ያደርጋል፤
  23. ውሳኔውን ለአልሚው ያሳውቃል እንዲሁም ደግሞ የቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ የፕሮግራም ለውጥ የሊዝ ውል ማሻሻያ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
  24. የተዘጋጀውን የሊዝ ውል በውል ሰጪና በውል ተቀባይ የፀደቀ መሆኑን ያረጋግጣል፤
  25. የጸደቀውን የሊዝ ውል ማሻሻያና ሌሎች ሰነዶዎችን እንዲደራጁ በማድረግ ለክፍለ ከተማ ያስልካል፡፤
  26. ለልማት የተላለፉ ቦታዎችን ዝርዝር መረከብና መለየት፣ በውላቸው መሠረት ያላለሙ አልሚዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ያስወስዳል፤
  27. በመስክ የክትትል ስራ እንዲሰራ በማድረግ መረጃ በማደራጀት የሊዝ ውላቸው እንዲቋረጥ የውሳኔ ሃሳብ እንዲዘጋጅ በማድረግ ለዳይሬክቶሬቱ ቀርቦ በዘርፍ ፕሮሰስ ካውንስል ቀርቦ ወይም ለቢሮ ስትራቴጂክ  ካውንስል እንዲቀርብ ያስደርጋል፡
  28. የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ሲጸድቅ የሊዝ ውሉ ተቋርጦ ቦታው መሬት ባንክ ገቢ እንዲሆን በሚመለከተው የስራ ክፍል እንዲፈጸም ውሳኔውን በማያያዝ እንዲያውቁት ለዳይሬክቶሬቱ ደብዳቤ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ያስደርጋል/ያደርጋል/ ያሳውቃል፡ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፣
  29. በሊዝ ውሉ መሠረት ግዴታቸውን ባልተወጡ አልሚዎች ላይ ክስ እንዲመሠረት መረጃ ተደራጅቶ ለአቃቤ ህግ መላኩን ይከታተላል፣ የፍርድ አፈፃፀሙን እስከመጨረሻው በመከታተል ተፈፃሚ እንዲሆን ያስደርጋል፤
  30. ከሊዝ ክፍያ ጋር ለሚቀርቡ ጥቄዎችና ቅሬታዎች ተቀብሎና አጣርቶ ምላሽ ይሰጣል/እንዲሰጥ ያደርጋል፣ የሊዝ ቅድመ ክፍያ እና የሊዝ ውል ማሻሻያ ቅጣት ማስከፈል እና የጊዜያዊ የሊዝ ውል ያለፈባቸውን ተከታትሉ መመለሱን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
  31. የተጣራውን ቅሬታ መረጃውን በማደራጀት የውሳኔ ሃሳብ እንዲዘጋጅ ያደርጋል/ያስደርጋል የተዘጋጀውን የውሳኔ ሃሳብ ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፤
  32. በሊዝ ምደባና በሊዝ ጨረታ ለተላልፉ ቦታዎች የሊዝ ቅድመ ክፍያ ገቢ መሆኑን ያጣራል፣ ሪፖርት ይቀበላል/ይከታተላል፣ ይገመግማል፤
  33. የአገልግሎት ለውጥ እና የፕሮግራም ለውጥ ቅድመ ክፍያ ገቢ መደረጉን እንዲሁም ከግንባታ ማራዘሚያ ቅጣት ጋር በተያያዘ በአግባቡ ክፍያው መፍጸሙን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፣ የሒሳብ ሰነዶች በሃርድና በሶፍት ኮፒ እንዲደራጁ ያስደርጋል፣
  34. የማጠቃለያ የሒሳብ ሪፖርት እንዲዘጋጅ ያደርጋል በዓመቱ መጨረሻ የሒሳብ ሰነዶች ኦዲት እንዲደረግ ጥያቄ ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ ለዳይሬክቶሬቱ ያሳውቃል፤
  35. በየክፍለ ከተማው በጊዜያዊ የሊዝ ውል የተላለፍ ቦታዎችን መረጃ እንዲሰበሰብ ያስደርጋል፤
  36. በተሰበሰበው መረጃ ላይ ተመስርቶ የጊዜያዊ መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው አልሚዎችን እንዲለዩ ያስደርጋል፣
  37. በተደራጀው ሰነድ መነሻነት የሊዝ ውል ጊዜያቸው ያለፈባቸውን አልሚዎች ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ለዳይሬክቶሬቱ የውሳኔ ሀሳብ በማዘጋጀት እንዲቀርብ ያደርጋል፣ ውሳኔ ሲያገኝ ቦታው ወደ መሬት ባንክ ገቢ እንዲሆን ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ውሳኔው እንዲደርሳቸው ያደርጋል ፤አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
  38. በየክፍለ ከተማው በሊዝ አፈጻጸም ዙሪያ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት የድርጊት መርሃ ግብርና ቼክሊስት በማዘጋጀት እንዲፀድቅ ያስደርጋል፤
  39. የሊዝ ክፍያ አሰባሰብ፣ የሊዝ ክትትል መስፈርት፣ስታንዳርድ፣ የአፈጻጸም ፎርማቶች እንዲቀረጹ፣ማሻሻያ ሲያስፈልግ በጥናት ተደግፎ እንዲቀርብ ያደርጋል፤
  40. በስራ ላይ ያሉትን የህግ ማዕቀፎችና የአሰራር ማኑዋሎች ያሉባቸውን ክፍተቶች ይለያል/እንዲለዩ ያደርጋል፤
  41. በሥራ ላይ ያሉትን አዋጆች፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን አስመልክቶ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በየክፍለ ከተማው የግንዛቤ መስጫ የውይይት መድረክ እንዲመቻች ያስደርጋል፤
  42. ከውይይት መድረኩ የተገኙ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየትና እንደግብዓት በመውሰድ ለቀጣይ ሥራ አደራጅቶ በሚመለከተው አካል ውሳኔ እንዲያገኝ ያቀርባል፤
  43. በሊዝ  የተላለፉ ቦታዎች በሊዝ ህጉ መሰረት በአግባቡ ልማት ላይ ስለመዋላቸው በስሩ ያሉ ባለሙያዎችን በማደራጀት ለክፍለ ከተሞች ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል ፤
  44. በሊዝ የተላለፉ ቦታዎችን መረጃ ከሚመለከተው አካል ይቀበላል፣ አደረጃጀቱን ይከታተላል፤
  45. ክትትል የሚደረግባቸውን የሊዝ ማህደራት እንዲለዩና መረጃው እንዲደራጅ ያደርጋል፤
  46. የግንባታ ደረጃ በመስክ እንዲከታተሉ በማድረግ ግንባታ በወቅቱ ባልጀመሩና ባላጠናቀቁ አልሚዎች ላይ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መሰጠቱን ይከታተላል፤
  47. ግንባታ የተጠናቀቀባቸውን ቦታዎች በሊዝ ውሉ መሠረት አገልግሎት መስጠታቸውን በመስክ እንዲከታተሉና ሪፖርት እንዲያቀርቡ ያደርጋል፤
  48. በውል ከተሰጠው አገልግሎት ውጪ አገልግሎት እየሰጠ ለሚገኝ ግንባታ ማስተካከያ እንዲያደርግ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ ያስደርጋል፤
  49. የሊዝ አመታዊና ውዝፍ ክፍያ ያለባቸውን ማህደራት እንዲለዩ በማድረግ ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ ክትትል ያስደርጋል፤
  50. በሊዝ ውሉ መሠረት ግዴታቸውን ላልተወጡ አልሚዎች ተለይተው እንዲቀርቡ እና የውሳኔ ሃሳብ እንዲዘጋጅ በማድረግ ላዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፤
  51. የጸደቀውን ውሳኔ ለሚመለከተው በማሳወቅ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤
  52. ከለማ መሬት ማስተላለፍ ቡድን በሚለካው ካቢኔ ውሳኔ መነሻ በማድረግና በሊዝ መመሪያ መሠረት የሊዝ ክፍያ አስልቶ እንዲያሳውቁ ይመራል፤
  53. የአልሚዎችን ልዩ ልዩ መረጃዎች በሶፍትና በሀርድ ኮፒ ከሊዝ ውሉ ጋር እንዲደራጁ ያደርጋልሸኝ ደብዳቤ በማዘጋጀት የተደራጀውን መረጃ ለክፍለ ከተማው እንዲላክ ያደርጋል፤
  54. የተሰበሰበውን ገቢ ለቢሮው ፋይናንስ ክፍል ፈሰስ መደረጉን ይከታተላል፡፡
  55. በየክፍለ ከተማ የሚከናወኑ ሥራዎች አሰራርን ተከትለው በአግባቡ ስለመተግበራቸው ይከታተላል፤
  56. ሌሎች ከሥራ ክፍሉ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን በበላይ ኃላፊ ሲመራለት ያከናውናል
  57. የስራ አፈጻጸም ይመዝናል፤ይገመግማል፤ክፍተቶችን ይለያል፤የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ አማራጮችንም በመለየት ተግባራዊ ያደርጋል፤