የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ

የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ

​​​​​​ የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት

ተጠሪነቱ ለመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡-

  1. ከክፍሉ ስትራቴጂ እና ዓመታዊ እቅድ በመነሳት የቡድኑን እቅድ እና ራስን የማብቃት ዕቅድ ያዘጋጃል፤
  2. ከስሩ ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር በዕቅዱ ዙሪያ ውይይት በማካሄድ የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር ያደርጋል፣ የቡድኑን ዕቅድ የመጨረሻ ቅርጽ አስይዞ ለበላይ ሀላፊዎች ያቀርባል፣ያስተቻል፣ያጸድቃል፣ እንዲተገበር ያደርጋል፡፡
  3. ለሥራ ክፍሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን (የሰው ኃይል፣ በጀት፣ ቁሳቁስ) እንዲሟላ  መረጃውን አደራጅቶ ለዳይረክቶሬቱ ያቀርባል፣በአግባቡ መሟላቱን ይከታተላል፣ያርጋግጣል፡፡
  4. በስሩ ያሉ  ባለሙያዎች የሥራ ዕቅድ ማዘጋጀቸውን፤ይከታተላል፣ይደግፋል፣ ያረጋግጣል፡፡
  5. ባለሙያዎች ያቀረቡትን የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ይመረምራል፣ይተቻል፣ ሪፖርቱ እንዲዳብር ድጋፍ ያደርጋል፣በየወቅቱ ይገመግማል፣ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡ ሪፖርቱን  ለቅርብ  ኃላፊው  ያቀርባል፡፡
  6. አገልግሎቱን ለመስጠት እንዲቻል ለባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታና የመሥሪያ ቁሳቁሶችን ያመቻቻል፣
  7. የቡድኑን ባለሙያዎች የአቅም ክፍተት በመለየት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
  8. በአመት ሁለት ጊዜ የቡድኑን ባለሙያዎች የስራ አፈጻጸም በመመዘን ውጤት ይሰጣል፣ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ባለሙያዎች ማበረታቻ እንዲሰጥ ያስተላልፋል ፡፡
  9. የክፍት ወይም ባዶ ቦታዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል መርኃ ግብር በማዘጋጀት በሚመለከተው አካል ያስጸድቃል ፡፡
  10. የክፍት ቦታዎችን መረጃ ከጂ.አይ.ኤስ. (GIS) እና ከመስመር ካርታ (Line Map) ላይ ለመልቀም የሚያስችል የካርታ ማውጫ (Index Map) ያዘጋጃል/ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
  11. ክፍት የሆኑ ቦታዎችን በጂ.አይ.ኤስ. ካርታ፣ከመስመር ካርታና ከቤዝ-ማፕ እንዲለይ ያደርጋል፡፡
  12. ክፍት የሆኑ ቦታዎችን ስኬች ይሰራል/ ያሰራል፤ባንክ መመዝገቡን ያረጋግጣል፡፡
  13. በባንክ የተመዘገበን መሬት በቤዝ ማፕ ያወራርሳል፤ወጭና ቀሪውን ያቀናንሳል/እንዲቀናነስ  መረጃውንም ያደራጀል፡፡
  14. ለመሬት ዝግጅት ሽንሻኖ እንዲሰራ ይልካል፡፡
  15. ለመሬት ዝግጅት ቡድን እንዲዘጋጅ ከተላከው ውስጥ ለልማት ያልተሸነሸነ ቀሪ መሬት በመረከብ፣ እንዲመዘገብ  ያደርጋል፡፡
  16. ተገቢ ባልሆነ አግባብ ይዞታዬ መሬት ባንክ ገባብኝ ለሚሉ አቤቱታዎች አጣርቶ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፡፡
  17. ክፍት የሆኑና ከማንኛውም አይነት የይገባኛል ጥያቄ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጡ ቦታዎች መረጃ አደራጅቶ እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡
  18. ጥበቃ እየተደረገላቸው የሚገኙ ቦታዎች በህጋዊ መንገድ ለልማት ሲተላለፉ አስፈላጊው ክትትል ተደርጎ የመረጃ ቋቱ ወቅታዊ ስለመደረጉና በመሰረታዊ ካርታ ላይ ስለመወራረሱ ክትትል ያደርጋል፡፡
  19. የመሬት ጥበቃ ሂደትን ለመከታተል የሚያስችል የሱፐርቪዥን እቅድ ያዘጋጃል፤ በሱፐርቪዥን ማከናወኛ ቼክ ሊስት መሰረት ሂደቱን ሱፐርቫይዝ ያደርጋል፤መረጃ አደራጅቶ ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡
  20. የመሬት ጥበቃ ስራ ላይ የሚታዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን ይገመግማል፣ ክፍተቶች ይለያል፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ እንዲፈቱ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፡፡ 
  21. የህገ-ወጥ መሬት ወረራ ጥቆማ ትክክለኛ ሆኖ ሲገኝ ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጋር በመተባበር ቦታው ለመንግስት ተመላሽ እየተደረገ ስለመሆኑ ይከታተላል፣መረጃው አደራጅቶ ለዘርፍ አሰተባባሪው ያቀርባል፡፡
  22. የክትትል እና ድጋፍ ድርጊት መርሃ-ግብርና ቼክሊስት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ያስፀድቃል፡፡          
  23. በተዘጋጀው መርሀ ግብርና ቼክሊስት መሰረት የድጋፍና ክትትል ሥራ ያከናውናል፡፡
  24. በድጋፍና ክትትል ስራ የተገኘው ግኝት መረጃ ያደራጃል ፤ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡