የመሬት ዝግጅትና መሰረተ ልማት አቅርቦት
የመሬት ዝግጅትና መሰረተ ልማት አቅርቦት ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት
ተጠሪነቱ ለመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡-
- ከክፍሉ ስትራቴጂ እና ዓመታዊ እቅድ በመነሳት የቡድኑን እቅድ እና ራስን የማብቃት ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡
- ከስሩ ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር በዕቅዱ ዙሪያ ውይይት በማካሄድ የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር ያደርጋል፣ የቡድኑን ዕቅድ የመጨረሻ ቅርጽ አስይዞ፣ያጸድቃል ፡፡
- ለሥራ ክፍሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን (የሰው ኃይል፣ በጀት፣ ቁሳቁስ) እንዲሟላ መረጃውን አደራጅቶ ለዳይረክቶሬቱ ያቀርባል፣በአግባቡ መሟላቱን ይከታተላል፣ያርጋግጣል፡፡
- በስሩ ያሉ ባለሙያዎች የሥራ ዕቅድ ማዘጋጀታቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ያረጋግጣል፤ የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ይመረምራል፣ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡
- የቡድኑን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፣ለባለሙያዎች አቅርቦ ያስተቻል፡ሪፖርቱን ለቅርብ ኃላፊው ያቀርባል፡፡
- አገልግሎቱን ለመስጠት እንዲቻል ለባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታና የመሥሪያ ቁሳቁሶችን ያመቻቻል፣
- ለትንሽ መስፈርትና ለትልቅ መስፈርት ካርታዎች ስራ የሚረዱ የቅድመ ቅየሳ መረጃዎችንና ዶክመንቶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
- ውስብስብ የሆኑ የቅየሳ ስራዎችን ለማከናወን የቅየሳና የስሌት መሣሪያዎች በመምረጥ እንዲቀርቡ ያደረጋል፣
- የጂኦዲቲክ፣ የትንሽ፣የትልቅ መስፈርት፣ የከፍታና የአግድመት መቆጣጠሪያ ነጥቦች /አውታሮችን/ እንዲመሰረቱና፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያስደርጋል
- የቶፖግሪፊና የካዳስትራል ቅየሣ ሥራዎችን በተፈለገው የጥራት ደረጃ ጠብቆ ውስብስብ ስሌቶችን እንዲቀመሩ፣ ፕሮፋይል ክሮስ ሴክሽንና ሴክሽን ፕላኖችን እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
- የከፍታ፣ የአግድመት፣ የግራቪቲና የማግኒቲክ ልኬቶችን እንዲወሰዱ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
- ለትልቅ መስፈርት ካርታዎች ሥራ ለኘላን ዝግጅትና ለመሳሰሉት የመቆጣጠሪያ ወይም የመነሻ ነጥቦች በበቂ ሁኔታ እንዲመሠረቱ እና ኮንትሮል ፖይንቶች እንዲቋቋሙ ያደርጋል
- አዳዲስ የቅየሳ የአሰራር ስልቶችን በመቀየስ እንዲሻሻሉ እገዛ ያደርጋል ፣
- በባለሙያዎች የተከናወኑ የቅየሳ ስራዎችን ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣ ኤዲት ያደርጋል፣ ያርማል፣ ያስተካክላል፣
- አንድ ፕሮጀክት ተጀምሮ እስከሚያልቅ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት መሠራታቸውን ይመረምራል፣ ይከታተላል፣ ወቅታዊ ሪፖርት እንዲቀርብ ያደርጋል፣
- የቅየሳ ስራ የተሰራባቸዉን ቦታዎች በቤዝ ማፕ ተደራጅተዉ በመረጃ ቋት እንደያዝ ያደርጋል፡፡
- በየደረጃው ለሚከናወን የቦታ ሽንሻኖ የተዘጋጀውን የሽንሻኖ ስታንዳርድ የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፣
- ቅደም ተከተል ያዘጋጃል፣ የቦታ ሽንሻኖ ስራ ወጥነትና ተገቢነት ያለው መሆኑን ይከታተላል፣
- የሽንሻኖውን ፎርማት ይቀበላል፣ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲደረግ ያደርጋል፣
- ሽንሻኖው በተገቢው ሁኔታ መሰራቱን ለማረጋገጥ የሽንሻኖውን ፎርማት ከባለሙያዎች ይቀበላል፣
- ተዘጋጀው የቦታ ሽንሻኖ በመመሪያውና በፕላን መሰረት መሆኑን ያረጋግጣል፣ ተገቢውን ማስተካከያ ይወስዳል፣ ያስወስዳል፣
- የቦታ ሽንሻኖው ስራ በስታንዳርዱና በፕላን መሰረት የተሰራ መሆኑን ያረጋግጣል፣
- የመሬት የፍላጎት እና አቅርቦት ዳሰሳ ጥናቶችን ይመራል ፤አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፤
- በጥናቱ መሰረት ለሽንሻኖ እና መሬት ዝግጅት ስራ የመሬት ቅደም ተከተል መዘጋጀቱን ያረጋግጣል፤አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፤
- የቡድኑን ባለሙያዎች የአቅም ክፍተት በመለየት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
- ለድጋፍና ክትትል የሚረዱ ልዩ ልዩ ቅጾችን በማዘጋጀት በስሩ ለሚገኙ ቡድኖች ያስተላልፋል፤ተግባር ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤
- በቡድኑ አሰራር ላይ መወሰን ያልተቻሉ ጉዳዮችንና ሌሎች ቅሬታዎች ሲቀርቡ ተቀብሎ ይመረምራል ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወሰዳል፣
- የቡድኑን የስራ መስተጋብር /Interface/ ያዘጋጃል፣ ይፈራረማል፣ ከሌሎች ጋር ቅንጀታዊ አሰራር እንዲኖር ተገቢውን ሁሉ ያደረጋል፣ያረጋግጣል
- የቡድኑ የተግባር አፈጻጸም የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ እንዲሆን ይቃኛል፣ ያረጋግጣል፣