የመልሶ ማልማት

የመልሶ ማልማት

​​​​​​ የመልሶ ማልማት ጥናት ቡድን 

  1. የዳይሬክቶሬቱን እቅድ መሰረት በማድረግ የቡድኑን ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡
  2. በፀደቀው ዕቅድ መሰረት በቡድኑ ስር ለሚገኙ ባለሙያዎች ሥራ ቆጥሮ ይሰጣል፣ ያስተባብራል፣ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
  3. የከተማ ንድፍ ጥናት ዝክረ-ተግባር እንዲዘጋጅ በማድረግ እንዲጸደቅ ያደርጋል፤
  4. አገልግሎቱን ለመስጠት እንዲቻል ለባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታና የመሥሪያ ቁሳቁሶችን ያሟላል፤
  5. በቡድኑ ስር የሚገኙትን ባለሞያዎቸ የስራ አፈፃጸማቸውን በመከታተል፣ በመገምገም ተገቢውን  ግብረ መልስ ይሰጣል፤
  6. በአፈፃጸም ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ይሰጣል፣ በሥራ ክፍሉ መወሰን የማይቻሉ ጉዳዮችና ቅሬታዎች ሲኖሩ ለዳይሬክተሩ/ዘርፉ በማቅረብ ያስወስናል፤
  7. ለቅደም ተከተል ጥናት መነሻ የሚሆን ዝክረ-ተግባር እንዲዘጋጅ በማድረግ ያጸድቃል፤
  8. መልሰው ሊለሙ የሚችሉ ቦታዎችን ከፕላን አንጻር በሙያተኞች እንዲለይ ያደርጋል፤
  9. ሥራውን ለማሳለጥ የሚያስችል የተለያዩ የጥናት ቡድኖችን ያዋቅራል፤
  10. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በመልሶ ማልማት በተከለሉ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የልማት ተነሺዎችን በማወያየት የጥናት ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ያደርጋል፤
  11. የመረጃ መሰብሰቢያ ቼክሊስቶች በሙያተኛ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
  12. በተዘጋጀው መረጃ መሰብሰቢያ ቼክሊስት መሰረት መረጃዎችን በመጠይቅ፣ ባለድርሻ አካላት በማወያየት እንዲሁም በመስክ ምልከታ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፤ 
  13. የተሰበሰበውን መረጃ በአግባቡ ተደራጅቶ፣ ተጠናቅሮ እና ተተንትኖ ረቂቅ የጥናት ሰነድ እንዲዘጋጅ  ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
  14. የተዘጋጀውን የልማት ቅደም ተከተል የጥናት ሰነድ በባለድርሻ አካላት በማስገምገም  እና የሚሰጠውን አስተያየት እንዲካተትና ሙሉ ሰነድ እንዲሆን ይሰራል፤
  15. የተዘጋጀው የቅደም ተከተል ረቂቅ ሰነድ በዳይሬክቶሬቱ አቅራቢነት በዘርፉ አማካይነት ለቢሮ ቀርቦ እንዲወሰን ያደርጋል፤
  16. የጸደቀው ቅድም ተከተል መነሻ የአከባቢ ልማት ፕላንና ከተማ ንድፍ  ጥናት  ለማካሄድና በአጭር ጊዜ መልሶ መልማት የሚችሉ ቦታዎች ለመለየት ውሳኔ እንዲያገኙ ቢሮ ለከተማ ካቢኔ አቅርቦ እንዲያስወስን አስፈለጊውን ሰነድ አዘጋጀቶ ያቀርባል፤
  17. በከተማ ካቢኔ የጸደቀውን የልማት ቅድም ተከተል ውሳኔ መሰረት አካባቢ ልማት ፕለን እና የከተማ ንድፍ ጥናት ያስጠናል ወይም ያጠናል ፣
  18. የጥናት ቡድኑ ጥናት የሚካሄድበትን አካባቢ በፕላንና በመስክ ምልከታ እንዲለዩ ያደርጋል፤
  19. ለከተማ ንድፍ ጥናት የሚያስፈልጉ የመረጃ ዓይነቶችን እንዲለዩ ያደርጋል፤
  20. ለመረጃ ማሰባሰቢያ የሚሆኑ መሳሪያዎችን  /ቼክ ሊስት፣ መጠይቅ/ ያዘጋጃል፤
  21. በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ መሰረት መረጃው በክፍለ ከተማ ይሰበስባል ወይም ያሰበስባል ፡
  22. በይዞታው ላይ የማልማት ፍላጎት ያላቸውንና ቀድሞ በይዞታቸው ላይ  ለማልማት ፈቃድ የወሰዱትን ባለይዞታዎች ለጥናቱ ግብአት በሚሆን መልኩ መረጃው ተለይቶ እንዲደራጅ ያደርጋል፤
  23. የተሰበሰበው መረጃ በአግባቡ ተተንትኖ ለአርባን ዲዛይን የሚሆን ረቂቅ የጥናት ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
  24. የተዘጋጀውን ረቂቅ ሰነድ በመገምገምና በማስገምገም ጠቃሚ የሆነውን ግብዓት ሰነዱ ላይ በማካተት እንዲጣናቀቅ ያደርጋል፤
  25. የተጠናቀቀውን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የጥናት ሰነድ ለከተማ ንድፍ ጥናት ግብአት እንዲሆን ያደርጋል፤
  26. ቀደም ብለው የተዘጋጁ እና አሁን በስራ ላይ ያሉ ለከተማ ንድፍ ስራ የሚያገለግሉ  መሪ ፕላን፣ አካባቢ ፕላን ጥናት እና ሌሎችን የፕላን መረጃዎች በሀርድና በሶፍት ኮፒ በማሰባሰብ ለአጥኝው ቡድን ያቀርባል፤
  27. የከተማ ንድፍ የሚዘጋጅለት አካባቢ የአካባቢ ልማት ፕላን ከሌለው በሚመለከተው አካል እንዲዘጋጅ በመጠየቅ ዝግጅቱን ይከታተላል፤
  28. የቦታውን የአካባቢ ልማት ፕላን እና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናት ሰነድ ተቀብሎ የከተማ ንድፍ ለሚሰራው አካል ያስተላልፋል፤
  29. የመስክ ምልከታ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችንና ቼክሊስት በማዘጋጀት/Physical, Spatial and Environmental data/ መረጃ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፡፡
  30. የከተማ ንድፍ ዝግጅት የተሰበሰበውን መረጃ ተተንትኖ የመሬት አጠቃቀምና ከባቢያዊ ሁኔታ ክፍተቶችን እንዲለዩ ያደርጋል፤
  31. ለልማት የተመረጠው አካባቢ በቀጣይ ሊኖረው የሚገባውን ሚና ኅብረተሰቡን በማሳተፍ ይለያል፤
  32. ጥናት በሚካሄድበት አካባቢ ያለው ኅብረተሰብ በልማት ቦታው መልሶ የሚሰፍርበትን፣ የማልማት ፍላጎትና መብት ያላቸው የሚካተቱበትን እና በአካባቢው ልማት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን  ሁኔታ በጥናቱ በማመላከት ለተግበራዊነቱ የዲዛይን ስልት ይነድፋል፤
  33. የከተማ ንድፍ ጥናት ሊያሟላ የሚገባውን መስፈርት ያካተተ ዝርዝር ስታንዳርድ ሰነድ ያዘጋጃል፤
  34. የከተማ ንድፍ ጥናቱ የተነደፈውን ንድፍ ሊያሳካ የሚችል የቦታ አደረጃጀት፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የህንጻ ሞርፎሎጂ፣ ወዘተ የያዘ ዲዛይን በመሰራት ረቂቅ ዲዛይን እንደዘጋጅ ያደርጋል፤
  35. ከዳይሬክተሩና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የከተማ ንድፍ ጥናት ላይ ከአከባቢ ነዋሪ ህብረተሰብ እና ባለድርሻ አካለት በመወያየት የጥናት ግብአት ይሰበስባል
  36. የተዘጋጀውን ረቂቅ የከተማ ንድፍ ጥናት ላይ ከኅብረተሰቡ እና በሚመለከታቸው አካላት በማስገምገምና የሰበሰበውን ጠቃሚ የሆነውን ግብዓት በማካተት ጥናቱ አጠናቆ ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፤
  37. የመጨረሻ የጥናት ሰነድ ሃርድና ሶፍት ኮፒ አደራጅቶ እንዲጸድቅ ለከተማ ፕላን ልማት ቢሮ እንዲላክ አዘጋጅቶ በዳይሬክቶሬቱ በኩል ለዘርፉ ያቀርበል፤ 
  38. የጸደቀውን ንድፍ ወይም ዲዛይን ሙሉ ሰነድ፣ ፕላኖች፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናቱን በሀርድና በሶፍት ኮፒ ትግበራው ለሚያካሂደው ቡድን ወይም አካል ያስተላልፋል፡፡
  39. የከተማ ንድፍ ሥራ በቡድኑ ባለሙያዎች የማይሰራ ከሆነ በውጪ አማካሪ ወይም ለከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ አስፈለጊው ዝክረ ተግባር አዘጋጀቶ ያቀርበል
  40. የከተማ ንድፉ ሊያሟላቸው የሚገቡ ውጤቶችና ሊያሳካቸው የሚገቡ ዓላማዎችን ይለያል፤
  41. የጨረታ ሰነድ  እና የስምምነት ሰነድ /ውል/ እንዲያዘጋጅ ያስደርጋል፤
  42. የአርባን ዲዛይን ባለሙያዎችና የጨረታው ሂደት የሚመለከታቸው አካላት ያሳተፈ የጨረታ ኮሚቴ በማቋቋም ጨረታ እንዲወጣና አሸናፊ እንዲለይ ያደርጋል፤
  43. ዝርዝር ቴክኒካል የአፈፃፀም መመሪያ/Guid-Line/ እንዲዘጋጅ አዲርጎ በማስገምገምና ግብዓቱን በማካተት አስጸድቆ ለጨረታ አሸናፊ እንዲደርሰው ያደርጋል፤
  44. ከጨረታ አሸናፊው ጋር ውል ስምምነት ይፈራረማል፤
  45. የከተማ ንድፍ ዝግጅቱ በጸደቀው ዝክረ-ተግባር እና በተዘጋጀው ቴክኒካል አፈፃፀም መመሪያ መሰረት እንዲከናወን ይከታተላል፤
  46. የከተማ ንድፍ ጥናቱ ሲጠናቀቅ የመጀመርያውን ረቂቅ ሰነድ በተቋሙ አመራሮች፣ በባለድርሻ አካላትና በልማት ክልሉ ነዋሪ በተወከሉ የህብረተሰብ አባላት ያስገመግማል፤
  47. በግምገማው የተገኙ ጠቃሚ ግብአቶች በማካተትና በማስተካከል ጥናቱ እንዲጠናቀቅ ክትትል ያደርጋል፤
  48. የተጠናቀቀውን የከተማ ንድፍ ጥናት  በውሉ መሰረት የተሟላ መሆኑን አረጋግጦ በመረከብ እንዲጸድቅ ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፤
  49. የጸደቀውን ንድፍ ሙሉ ሰነድ /ፕላኖች፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናቱን/ በሀርድና በሶፍት ኮፒ በማደራጀት በጥናቱ በተቀመጠው የአተገባበር ስልት መሰረት እንዲፈጸም ትግበራው ለሚያካሂደው ቡድን ወይም አካል ያስተላልፋል፤
  50. የቡድኑን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በየወቅቱ ለዳይሬክቶሬቱ አዘጋጅቶ ያቀርባል