ክስተቶች

ክስተቶች Training

image description
የመጀመሪያ ቀን icon
የመጨረሻ ቀን icon
አካባቢ የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

value="

በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልማት ተነሺዎች መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ለሸገር ወንዝ ዳርቻ ልማት ምክንያት ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ለተነሱ 124 የልማት ተነሺዎች የክህሎት ስልጠና በቴክኒክ ፖሊ ኮሌጅ እየሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናውን  የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልማት ተነሺዎች መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ከቴክኒክ ፖሊ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ያዘጋጀ ሲሆን የልማት ተነሺዎቹ በመረጡት የሙያ ዘርፍ ለአንድ ወር የሚቆይ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና እንደሚሰጥ ተጠቅሷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልማት ተነሺዎች መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በየነ ላምቢሶ ቢሮው ለመንግስትና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከተለያዩ የከተማዋ ክፍል የሚነሱ የልማት ተነሺዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲያዘጋጅ መቆየቱን ጠቁመው በመጀመሪያ ዙር ከጉለሌ እና አራዳ ክፍለ ከተሞች በሸገር ወንዝ ዳርቻ ምክንያት ለተነሱ የልማት ተነሺዎች ራሳቸውን የሚያበቁበትና ለስራ ዝግጁ የሚሆኑበት የክህሎት ስልጠና ይሠጣል ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም የተዘጋጀውን የክህሎት ስልጠና በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁ ስልጣኞች በቀጣይ በማህበር ተደራጅተው በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ  ሰርተው ራሳቸውን እንዲለውጡ ከወለድ ነፃ ብድርና መስሪያ ቦታ ይመቻቻል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልማት ተነሺዎች መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ለመንግስትና ህዝብ ጥቅም ሲባል ከተለያዩ የከተማዋ ክፍል የሚነሱ የልማት ተነሺዎችን በዘላቂነት የሚያቋቁም የስራ ክፍል ነው፡፡

"

  • icon 9:30am - 1:00pm
  • የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

Related Events