ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 162/2ዐ16 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሻሻለ የከተማ መሬት ሊዝ ደንብ

image description

መሬት ለአንድ ሀገር ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ የሆነ ሀብት እንደመሆኑ መጠን መንግሥት ይህንን ውስን ሀብት ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነትን ባሰፈነ አሠራር ጥቅም ላይ መዋሉን ማረጋገጥ የሚያስፈልግ በመሆኑ፤
የከተማ አስተዳደሩን የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እና ግልጽ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት በመሬት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ የሚስተዋሉ የአሰራርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ዕልባት መስጠት በማስፈለጉ፤
የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ በማጥናት ወደ ስራ የተገባ በመሆኑ አገልግሎት እየተሰጠባቸው የሚገኙት ደንብና መመሪያዎች ከተደረጉት የአደረጃጀት ለውጦች ጋር የተናበቡ መሆን ስላለባቸውና የከተማው ዕድገትን ተከትሎ የመጣ የልማት ፍላጎት እድገት በመኖሩ፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ሥራ ላይ ያጋጠሙ የአሰራር ችግሮች መፍትሔ መስጠት በማስፈለጉ፤
በሥራ ላይ በነበሩ ህጎች ላይ የሚስተዋሉ የተናባቢነትና የግልጸኝነት ችግሮች እና ህዝቡ የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መልስ ለመስጠት እና በውሳኔ አሰጣጥ እንዲሁም በአፈጻጸም ሂደት በደንብ እና መመሪያዎች ላይ ላጋጠሙ ችግሮች የማብራሪያና ሰርኩላሮች መብዛት እርስ በራስ የሚጋጩ ውሳኔዎችን ዘላቂ መፍትሄ በመስጠት ግልጽና ወጥ የሆነ የሊዝ ደንብ ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ፤
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 23 ንዑስ አንቀፅ (1) ተራ ፊደል (ረ) እና የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 33 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡