ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 163/2016 የመሬት ይዞታ መብት ፈጠራ እና አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ

image description

የከተማው አስተዳደር በመሬት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ የሚስተዋሉ የአደረጃጀት፣ አሰራር እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ዕልባት ለመስጠት ለበርካታ ጊዜያት የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ በማጥናት ወደ ስራ የተገባ ቢሆንም አገልግሎት እየተሰጠባቸው የሚገኙት በርካታ መመሪያዎች ከተደረጉት የአደረጃጀት ለውጦች ጋር የተናበቡ ባለመሆናቸው እና መመሪያዎቹ በተበታተነ መልኩ የሚገኙ በመሆናቸው በውሳኔ አሰጣጥ፣ በስራ ቅብብሎሽ በአጠቃላይ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ችግሮች በማጋጠማቸው፤ ችግሮቹን መፍታት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ችግሮቹን በማብራሪያና ሰርኩላር የመፍታት ጥረት የተደረገ ቢሆንም ማብራሪያውና ሰርኩላሩ ከመብዛታቸው በተጨማሪ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩበት ሁኔታ ስለተከሰተ የህግ ማዕቀፉን ማስተካከል በማስፈለጉ፣
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 33 ንዑስ አንቀጽ (2) እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር የመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 94 መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡