ህትመቶች

በሶስተኛው ዙር ሁለተኛ የወጣችሁ ተጫራቾች ከጷጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሊዝ ውል እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በአዲስ ከተማ፣ በጉለሌና በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ መውጣቱና ከነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአንደኛ አሸናፊዎች ጥሪ ተደርጎላቸው የሊዝ ውል መወያያው ጊዜ የተጠናቀቀ በመሆኑ በሊዝ ደንቡ መሰረት ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘራችሁ ሁለተኛ የወጣችሁ ተጫራቾች ከጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርባችሁ የሊዝ ውል እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ