ህትመቶች

4ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማራዘምን ይመለከታል

4ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማራዘምን ይመለከታል 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተያዘው በጀት ዓመት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመፍቀድ በወጣው የሊዝ አዋጅ 721/2004 መሰረት በ4ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጪ በ10 ክፍለ ከተሞች  ከመገናኛ ቦሌ ኤርፖርት መንገድ፣ ከመገናኛ ሲኤሚሲ፣ ከመገናኛ አራት ኪሎ ፣ እንዲሁም ጎተራ አከባቢ  285 ፕሎቶችን  በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማሳተም ከጥቀምት 08/2017 እስከ ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጅ የጨረታ ሰነድ ሽያጩን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም እሰከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት የቴሌ ብር አካውንት በመክፈት ከአካውንታችሁ ተቀናሽ በማድርግ ክፍያ በመፈፀም የጨረታ ሰነዱን (addisland.2merkato.com ወይም addisland.afrotender.com) በመግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባችዋል።
ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ፣ የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበትን ስሊፕና ሌሎች በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን ጭምር በኤንቨሎፕ በማሸግ ህዳር 05/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ብቻ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ቦታዎችን ጥቅምት 25፣27 እና 29 / 2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 እና ከሰዓት 8፡00 በየክፍለ ከተማው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት መጎበኘት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 06/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ  የሚከፈት  ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገልፅ  ይሆናል።

የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ጥቅምት 08/2017 በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይችላሉ።መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ስልክ ቁጥር +251 111570595 መደወል ይችላሉ፡፡