ለ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ከ300 በላይ ቦታዎች ተዘጋጅቷል፡፡
ለ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ከ300 በላይ ቦታዎች ተዘጋጅቷል፡፡
ለ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ከ300 በላይ ቦታዎች ተዘጋጅቷል፡፡
የሰነድ ሽያጭ ስራው ከመጋቢት 1 እስከ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
የካቲት 28/2017 (መልአቢ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የህብረተሰቡን የመሬት ፍላጐት ለማሟላት ተከታታይ የመሬት ሊዝ ጨረታ ሲያወጣ መቋየቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሠረት ቢሮው በ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተዘጋጁ ከ300 በላይ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቋል፡፡
የሰነድ ሽያጭ ሥራው ልክ እንደዚህ ቀደሙ ከእጅ ንክኪ በፀዳ መልኩ ከመጋቢት 1 ቀን እስከ ከመጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት በhttps://addisland.2merkato.com እና https://addisland.afrotender.com በኦላይን የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተከታታይ 5 የሥራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሚታተመው አዲስ ልሳን ጋዜጣ መመልከት ይችላሉ፡፡
መልካም ዕድል!
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ