ህትመቶች

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያወጣዉን የመሬት ሊዝ ጨረታ በጨረታዉ የተሰረዘ ቦታን ይመለከታል

1.  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ  አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም  አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ኮልፌ ቀራንዮ ፤በአቃቂ ቃሊቲ፤በየካ፤ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ ፣በቂርቆስ፣በጉለሌ፣እና በልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ሚያዚያ 09/2016ዓም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማሳተም ከሚያዚያ 10/2016ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 24/2016ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጅ የጨረታ ሰነድ ሽያጩን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከ28/2016ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/09/2016ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሽያጩ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፡-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት የቴሌ ብር አካዉንት በመክፈት ከአካዉንታችሁ ተቀናሽ በማድረግ ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን በ(2merkato.com link:- https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) በመግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ  መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ፣የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ግንቦት 09/2016ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 9 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ  የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
2.  በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 01 ለጨረታ ከወጡት ቦታዎች ዉስጥ የቦታ  ኮድ LDR-AKI-MIX-00013138 የቦታ ስፋት 390ሜ.ካ የሆነ ቦታ ከጨረታ የተሰረዘ መሆኑን እየገለጽን  
የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሚያዝያ 09/2016 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡ 
ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ በስልክ ቁጥር +251111566440 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ 
በድህረ ገፅ https://www.aalb.gov.et መመልከት ይችላሉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ