ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾች ውል እንዲዋዋሉ ስለመጠየቅ
ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ፣ በጉለሌ እና በልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ መውጣቱና ከግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ አንደኛ የወጡ አሸናፊዎች ጥሪ ተደርጎላቸው የመዋዋያው ጊዜ የተጠናቀቀ በመሆኑ በሊዝ ደንቡ መሰረት ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረው ሁለተኛ የወጣችሁ ተጫራቾች ከ14/10/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለው 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለም ሆቴል በሚገኘው ቢሮ ቀርባችሁ የሊዝ ውል እንድትፈጽሙ እናሳውቃለን ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ