ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በቅርቡ 2ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፉ ይታወሳል ፡፡
በዚሁ መሰረት ተቋማችን የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የህበረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡በመሆኑም ቢሮው የመሬት ሊዝ ጨረታ ለማውጣት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን እየገለፀ የጨረታ ዝርዝር መረጃውን ቅዳሜ 29/2016 ዓ.ም በሚወጣው አዲስ ልሳን ጋዜጣ የሚገለጽ መሆኑን እያሳወቅን በዚሁ አጋጣሚ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ ያሳውቃል ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ